ፍራንዝ ቤከንባወር ከዚህ አለም በሞት ተለየ!

የቀድሞው የምዕራብ ጀርመን እና የባየርሙኒክ ኮከብ ፍራንዝ ቤከንባወር በ78 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ቤከንባወር በ1974 ጀርመን የዓለም ዋንጫን ስታነሳ ብሄራዊ ቡድኑን በአምበልነት መምራት የቻለ ሲሆን ÷በ1990 ደግሞ የጀርመን ብሄራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት እየመራ የዓለም ዋንጫን ማንሳት ችሏል፡፡

ባለ ተሰጥዖ ተከላካይ እንደሆነ የሚነገርለት ፍራንዝ ቤከንባወር በምዕራብ ጀርመን ብሄራዊ ቡድን 104 ጨዋታዎችን ማሸነፍ መቻሉ ተገልጿል፡፡

በቀድሞው ተጫዋች ህልፈት ጀርመናውያን፣የቡድን አጋሮቹ እና አለምአቀፉ የስፖርት ቤተሰብ ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe