ፑቲን በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ ክልከላ የሚያደርግ አካል ከራሺያ ጋር ቀጥተኛ ጦርነት ይገጥማል ሲሉ አስጠነቀቁ!

የራሺያው ፕረዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሀገራቸው ብሔራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈው መልዕክታቸው እንዳሉት በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ እቀባ(No Fly Zone) የመጣል እቅድ ያላቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፤ ካልሆነ ግን በጦርነቱ ቀጥታ እየተሳተፉ መሆናቸውን ይወቁ ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት የዩክሬን ባለስልጣናት ኔቶ በዩክሬን ከበረራ ነፃ ቀጠና እንዲፈጥር መወትወታቸው ከተሰማ በኋላ ነዉ። ምንም እንኳን የኔቶ ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ በዩክሬን የበረራ እቀባ መጣል ማለት የራሺያን የጦር ጄቶች በቀጥታ መትቶ መጣል እንደማለት ስለሆነ ይህን ማድረግ ጉዳዩን ያወሳስበዋል በማለት ይህንን እንደማያደርጉ ቢገልፁም።ዘገባው የዘ ቴሌግራፍ ነዉ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe