ፓተንት ያገኙ የፈጠራ ባለቤቶች የባንክ ብድር ሊሰጣቸው ነው

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 19 ቢሊዮን ብር አዘጋጅቷል

የባለቤትነት ማረጋገጫ (ፓተንት) ያገኙ አዳዲስ የፈጠራ ባለቤቶችን በገንዘብ ለመደገፍ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አስታወቀ።

ባንኩ የፈጠራ ሃሳቦችን ፋይናንስ በማድረግ የፈጠራ ባለቤቶቹን ወደ ኢንቨስትመንት ለማስገባት መዘጋጀቱን ነው ያስታወቀው።የአገሪቱን የኢንቨስትመንት ፍላጎትና የባንኩን ተልዕኮ ያጣጣመ የቢዝነስ ሞዴል መዘጋጀቱም ባንኩ ጠቁሟል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሃንስ አያሌው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ባንኩ በተያዘው ዓመት 19 ቢሊዮን ብር ብድር ለማቅረብ እየሰራ ይገኛል።ከዚህ ቀደም የተለያዩ የብድር አይነቶችን ሲያቀርብ መቆየቱን ገልጸው፤ አሁን ደግሞ አዲስ የፋይናንስ አቅርቦት ለመጀመር ተዘጋጅቷል ብለዋል።

ይህም አዳዲስ የፈጠራ ኃሳቦችን ፋይናንስ የሚያደርግ መሆኑንና ይህንን ሥራ የሚያካሂድ ራሱን የቻለ ክፍል እንደተቋቋመለት ጠቁመዋል። በተበላሸብድር ሳቢያ ባለፉት ዓመታትኪሳራ ለይ የከረመው ባንኩ ቀልጣፋና ግልፅነት ያለው አሰራርን በመከተል  ባለፈው ዓመት3 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ገልፀዋል።

SourceReporter

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe