ፓኪስታን ለየትኛውም ከህንድ ለሚቃጣ ወረራ ምላሽ ለመስጠት በተጠንቀቅ ላይ እንደምትገኝ ገለጸች

ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር እሁድ እለት በአሜሪካ ከሚገኙ የፓኪስታን ዳያስፖራዎች ጋር በነበራቸው ውይይት ይህን ብለዋል፡፡ ፊልድ ማርሻል ሙኒር በፓኪስታን ላይ የሚቃጣ ጦርነት ግማሽ የዓለምን ክፍል አብሮ የሚያጠፋ ነው ብለዋል፡፡ ፓኪስታን ኒውክሌር ታጣቂ አገር በመሆኗ በእኛ የሚደረግ ጦርነት በሙሉ እኛን ብቻ ሳይሆን ግማሽ የሚሆነውን የዓለምን ክፍል አብሮ ቁልቁል ይዞ የሚወርድ ነው ሲሉ በአሜሪካ በነበራቸው ጉዞ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር ህንድ በኢዶስ ወንዝ ላይ የምትገነባውን ግድብ እስክትጀምረው ነው የምንጠብቀው የሚሳኤል እጥረት የለብንም በማለት ፓኪስታን ምን ለማድረግ እቅድ እንዳላት አመላክተዋል፡፡ ግድቦችን ማጥቃት የጦር ወንጀል መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሙኒር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀናት ወደ አሜሪካ ያቀኑት ወዳጃቸው በሆኑት  የአሜሪካ የሴንተራል ኮማንድ ኮማንድር የሆኑትን ማይከል በጡረታ የሚገለሉበትን ስነ ስርዓት ለመታደም ነበር፡፡

ከዚሁ ስነ ስርዓት በተጓዳኝ ከፓኪስታን ዲያስፖራዎች ጋር በዝግ በተገናኙበት ወቅት ነው ይህን ማለታቸው የተገለጸው፡፡

ህንድ እንዲህ አይነት አደገኛ መልዕክቶች በሦስተኛ ወዳጅ ሀገራት ላይ መሰማቱ እንዳሳዘናት ገልጻለች፡፡ በተጨማሪም ብሔራዊ ደህንነቷን ለማረጋገጥ የምታደርጋቸውን አስፈላጊ እርምጃዎች እንደምትቀጥል አስታውቃለች፡፡ የፓኪስታኑ የጦር ሰው ስለ ኒውክሌር ስጋት በአሜሪካ ተገኝተው እንዲህ አይንነት መልዕክት ማስተላለፋቸውን በተመለከተ አሜሪካ ምንም አለማለቷም ትክክል እንዳልሆነ ህንድ ገልጻለች፡፡ ኒውክሌር ታጣቂ አገራት የኒውክሌር ጦር መሳሪያውን የሚቆጣጠረው በህዝብ የተመረጠው ሲቪሊያን አስተዳደር ነው ያለችው ህንድ  በፓኪስታን ግን ይህን የሚቆጣጠረው ወታደሩ ነው ብላለች፡፡ ከፓኪስታን ወታደር በኩል የተሰማው ንግግር ደግሞ ስጋቱን ከፍ የሚያደርገው ሆኗል፡፡

በዚህ ከፊልድ ማርሻሉ አሲም ሙኒር የአሜሪካው ቆይታቸው በኋላ በህንድ እና በፓኪስታን መካከል አዲስ ውጥረት ስለመምጣቱ እየተገለጸ ነው፡፡ ኢስላማ ባድ በኢንዶስ ወንዝ ያላትን ጥቅም ለማስከበር የትኛውንም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆኗንም ገልጸዋል፡፡ የኢንዶስ ወንዝ የህንድ የቤተሰብ ንብረት አይደለም ያሉት ፊልድ ማርሻሉ ሙኒር ይህንን ተላልፋ ግድብ የምትገነባ ከሆነ ያለማወላወል እንመታዋለን ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ በተጨማሪም የካሽሚር ጉዳይ መፍትሔ ያልተሰጠው ዓለም አቀፍ ጉዳይ እንጂ የህንድ የውስጥ ጉዳይ አይደለም ብለዋል፡፡ ህንድ እና ፓኪስታን ከወራት በፊት ለአራት ቀናት የዘለቀ ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡//

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe