ፓኪስታን በድንበር አካባቢ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 70 ታጣቂዎችን መግደሏን አስታወቀች

የአፍጋኒስታን ባለስልጣናት የፓኪስታንን የይገባኛል ጥያቄ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፤ፓኪስታን ሲቪሎችን ኢላማ አድርጋለች እንዲሁም የአገሪቱን ሉዓላዊነት ጥሳለች ሲሉ ከሰዋል፡፡
በሁለቱ ጎረቤት አገራት መካከል እየተባባሰ በመጣው ውጥረት ውስጥ የፓኪስታን መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ወታደሮቻቸው በአፍጋኒስታን ድንበር አቅራቢያ በፈጸሙት የአየር ጥቃት 70 ታጣቂዎችን መግደላቸውን ተናግረዋል፡፡
የፓኪስታን የመረጃ ሚኒስትር በኤክስ ገጻቸው ላይ ወታደራዊ ሃይሉ በታሊባን እና አጋሮቹ በሚጠቀሙባቸው ሰባት ካምፖች ላይ በመረጃ የተደገፈ እና የተመረጠ ኦፕሬሽን ማከናወኑን ጽፈዋል፡፡
ሚኒስትሩ ፓኪስታን ሁሌም በክልሉ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን እንደምትጥር ገልጸው ነገር ግን የዜጎቿ ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ፓኪስታን በአፍጋኒስታን የሚገኘው የታሊባን መንግስት ታጣቂዎች የአፍጋኒስታንን መሬት ለጥቃት እንዳይጠቀሙ ደጋግማ ብትጠይቅም ካቡል ግን ምንም አይነት ተጨባጭ እርምጃ አልወሰደችም በማለት ትከሳለች፡፡
አፍጋኒስታን በበኩሏ የሚቀርብባትን ክስ ውድቅ አድርጋለች፡፡ መከላከያ ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ የተፈጸመው ጥቃት የሀገሪቱን የአየር ክልል እና ሉዓላዊነት የጣሰ ተግባር ሲል አውግዞታል፡፡
የታሊባን መንግስት ቃል አቀባይ ፓኪስታን የሰዎችን መኖሪያ ቤት በማፍረስ፡ሲቪሎችን ኢላማ በማድረግ ወንጀል ፈጽማለች ብለዋል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe