ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራን ጦርነቱን ለማጠናቀቅ ከአሜሪካ የቀረበውን እቅድ እየተመለከተችው ነው አሉ

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከቴህራን ጋር ያለው የድርድር ሂደት ጥሩ ውጤት እያሳዬ ነው አሉ። በዚህ ስዓት በሁለቱም ወገኖች ከስምምነት ለመድረስ ፍላጎት አለ ብለዋል።
ዋሽንግተን ባለፉት 24 ስዓታት ውስጥ በጣም ጥሩ የሚባል ንግግር ከቴህራን ጋር አድርጋለች ብለዋል።
ኢራን ደግሞ ጦርነቱን ለማጠናቀቅ ከአሜሪካ የቀረበውን እቅድ ተመልክተዋለች ብለዋል። እናም አሁን ወደ ስምምነት የሚደረስበት በጣም ጥሩ እድል አለ ሲሉ ትላንት ዕረቡ በኦቫል ኦፊስ ለሪፖርተር ገልጸዋል።
ነገሮች በጣም ጥሩ በሚባል ደረጃ እየሄዱ ነው፤ወደፊት ደግሞ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አብረን እናያለን ነገር ግን ኢራናውያን መደራደር እንዲሁም ከስምምነት መድረስ ይፈልጋሉ ብለዋል።
ኢራን እና አሜሪካ በዚህ ስዓት በአሸማጋዮች በኩል ጦርነቱን ሊያስቆም እንዲሁም የሆርሙዝ ሰርጥን እንዲከፈት የሚያስችል ንግግር ዳግም እንዲጀመር ይፈልጋሉ።
ይሄው ተጠባቂው ዳግመኛ ንግግርም በመጪው ሳምንት በኢስላማባድ ሊደረግ መታቀዱን ዎልስትሪት ጆርናል ጽፏል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕም በመሆኑ ከኢራን ጋር ያለው ሁኔታ በቀጣይ ሳምንት ወደ መጠናቀቅ እንደሚመጣ እምነት እንዳላቸው ለFOX NEWS ገልጸዋል።
ትላንትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርክ ሩቢዮ ኢራን ላይ የተጀመረው የኤፒክ ፉሪ ዘመቻ ግቦቹን በማሳካቱ ተጠናቋል ብለዋል።
በ April 8 በፓኪስታን አሸማጋይነት የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱ የሚታወስ ሲሆን፤ነገር ግን ይህ የኢስላማባዱ ስምምነት በሀገራቱ መካከል ያለውን ግጭት ሙሉ በሙሉ እንዲገታ ማድረግ አላስቻለም።
ፕሬዚዳንት ትራምፕም የተደረሰው የሁለት ሳምት ተኩስ አቁም ስምምነት ሲጠናቀቅ ይሄ የተባለ ቀነ ገደብ ሳያስቀምጡ ተኩስ አቁሙ እንዲራዘም አድርገዋል።
ማክሰኞ እለት ደግሞ አሜሪካ አስጀምራው የነበረው የፕሮጀክት ፍሪደም በጊዚያዊነት እንዲገታ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe