ፕሬዚዳንት ትራምፕ የዲቪ ሎተሪ ማመልከቻ እንዲቆም አዘዙ

አሜሪካ ላለፉት 30 ዓመታት በስራ ላይ የነበረውን የዲቪ ሎተሪን ማቆሟ ተገለጸ፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በብራውን ዩኒቨርሲቲ በተፈተመ የጅምላ ጥቃት ሁለት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዲቪን አግደዋል፡፡

ጥቃቱን ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረው እና ሀሙስ እለት ህይወቱ አልፎ የተገኘው ፖርቹጋላዊ በ2017 በዲቪ ሎተሪ ነበር ወደ አሜሪካ የገባው ተብሏል፡፡

አሜሪካ በየዓመቱ በምትሰጠው የዲቪ ሎተሪ እድል ከመላው ዓለም ለ55ሺ ሰዎች ቪዛ ትሰጥ ነበር፡፡ የትራምፕ አስተዳደር በዚህ ፕሮግራም አሜሪካዊያን እንደይጎዱ ለማረጋገጥ በሚል ፕሮግራሙን ለጊዜው እንዲቋረጥ አድርጎታል፡፡

በየዓመቱ ከ14 ሚሊዮን በላይ የሚደርሱ ሰዎች የዲቪ ሎተሪን እንደሚሞሉም መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን በ2025 20 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች አመልክተው ነበር ተብሏል፡፡

አሜሪካ ከአውሮፓዊያኑ 1995 ጀምሮ በደቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ አገሯ በርካቶች እንዲገቡ ስትፍቅድ ቆይታለች፡፡ በዚህ እድል አማካኝነትም ወደ አሜሪካ የገቡ ስደተኞች ቁጥር ወደ አንድ ሚሊዮን ይደርሳሉ ተብሏል፡፡

ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ ወዲህ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ የተለያየ እርምጃ እየወሰዱ ነው፡፡

በአሜሪካ ውስጥ የሚገኙ ሰነድ አልባ ስደተኞችንም ወደ መጡበት ለመመለስ ትኩረት አድርገው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሳምንታት አንድ የአፍጋኒስታን ስደተኛ በዋሽንግተን ዲሲ ሁለት የአሜሪካ ብሔራዊ ዘብ አባላትን በጥይት ተኩሶ አንዷን ከገደለ እና ሌላኛውን ካቆሰለ በኋላ የሀገሪቱ መንግስት ከ119 አገራት የመጡ ስደተኞች የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ ዳግም ፍተሻ እንደሚያደርግ ይፋ አድርጓል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe