ፕሬዝደንት አልበሽር ሱዳንን ከኤርትራ ጋር የሚያዋስነውን ድንበር ለመክፈት ጥረት እያደረጉ ነው፡፡

ፕሬዝደንት አልበሽር ከዓመት በፊት የተዘጋውን የኤርትራ ድንበር ለመክፈት ጥረት እያደረጉ ነው፡፡

የሱዳኑ ፕሬዝደንት ኡመር ሃሰን አልበሽር ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ የዘጉትን የኤርትራ ድንበር ለመክፈት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ትናንት አስታውቀዋል፡፡  ይህን የወሰኑትም ለስድስት ሳምንታት የዘለቀውን ተቃውሞ ለማብረድ ይመስላል ነው የተባለው፡፡

ለሦስት ዓስርት ዓመታት የዘለቀውን የአልበሽር አገዛዝ በመቃዎም ሱዳናውያን ጎዳና ላይ  ከወጡ ሰነባብተዋል፡፡ የሀገሪቱ የመከላከያ ኃይልም ትናንት ሃሙስ በርዕሰ መዲናዋ ካርቱም እና በሌሎች ከተሞች ጎዳና ላይ የወጡ ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙን የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዝደንት አልበሽር በኤርትራ ድንበር በምትገኘው ከሰላ ግዛት ትናንት ተገኝተው የኤርትራን ድንበር ዳግም ለመክፈት እየሰሩ መሆኑን ለደጋፊዎቻቸው ገልፀዋል፡፡ ‹‹የምገልፅላችሁ ነገር ቢኖር ከጎረቤት ኤርትራ ጋር የሚያገናኘው ድንበር ክፍት ይሆናል፤ ምክንያቱም ኤርትራዊያን ወንድሞቻችን ናቸው፤ፖለቲካ ሊከፋፍለን አይገባም›› ብለዋል አልበሽር በከሰላ ለተሰበሰቡት ደጋፊዎቻቸው፡፡

ሱዳን ከኤርትራ ጋር የነበራትን ድንበር የዘጋችው ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ በከሰላ እና በደቡባዊ ኩርዶፋን ለስድስት ሳምንታት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ ነበር፡፡

በሀገራቸው ህዝባዊ አመፅ በተቀሰቀሰበት የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት በኳታር እና በግብፅ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉት ፕሬዝደንት አልበሽር ከሳዑዲ አረቢያ እና ከኩዌት ድጋፍ ተችሯቸዋል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe