ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ስልጣናቸዉን እንዳይለቁ በህክምና ዶክተሮች ተጠየቁ

በዩጋንዳ የሚገኙ ዶክተሮች በጉልበታቸዉ በመንበርከክ 36 ዓመታት የመሩትን ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ስልጣናቸዉን እንዳይለቁ ጠየቁ

በዩጋንዳ የሚገኙ የህክምና ዶክተሮች ቡድን የረዥም ዓመታት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒን ተንበርክከው ለሰባተኛ የስልጣን ዘመን እንዲወዳደሩ የጠየቁ ሲሆን የህክምና ባለሙያዎቹ ድርጊት ዉዝግብ አስነስቷል፡፡

የ78 አመቱ መሪ ሙሴቬኒ ከ1986 ጀምሮ በስልጣን ላይ የሚገኙ ሲሆን በ2026 ዓመት በሚካሄደዉ ምርጫ እንዲወዳደሩ ተጠይቀዋል፡፡የዩጋንዳ የህክምና ማህበርን ወክለው የመጡት ሀኪሞች በዋና ከተማዋ ካምፓላ በአርበኝነት ሲምፖዚየም ላይ ተገኝተው በፕሬዝዳንቱ ፊት ተንበርክከው እንደነበር ዝግጅቱን የተከታተሉ የመገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

የዩጋንዳ የህክምና ማህበር ኃላፊ ዶክተር ሳሙኤል ኦዶንጎ ኦሌዶ ባደረጉት ንግግር ፕሬዝዳንቱ የሀገሪቱን የጤና ስርዓት በመለወጥ እና የህክምና ባለሙያዎችን ደህንነት በማሻሻል አመስግነዋል።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ እ.ኤ.አ. በ2026 ለፕሬዝዳንታዊ እጩነት በድጋሚ እንዲቀርቡሩ መጠየቁን ኤንቲቪ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe