ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደቡብ አፍሪካ ከቡድን 20 አባልነት መውጣት አለባት ብለው እንደሚያምኑ ገለጹ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደቡብ አፍሪካ ከቡድን 20 አባልነት መውጣት አለባት ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

ደቡብ አፍሪካ የቡድን 20 ጉባኤን ለማስተናገድ ዝግጅት እያደረገች ባለችበት ወቅት ነው ትራምፕ ይህንን ያሰሙት፡፡

በያዝነው ወር መጨረሻ ላይ የዓለም ትልልቅ ምጣኔ ሃብት ያላቸው አገራት በጆሀንስበርግ እንደሚገናኙ ይጠበቃል፡፡

ደቡብ አፍሪካ ነጮች ላይ መድሎ ታደርሳለች ብለው በተደጋጋሚ የከሰሱት ትራምፕ በጉባኤው እንማይገኙና በምትካቸው ምክትላቸው ጄዲ ቫንስን እንደሚልኩ ተናግረዋል፡፡

ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ጉባኤውን የምታዘጋጀው አሜሪካ ናት፡፡ ደቡብ አፍሪካ የቡድኑ አባል መሆን የለባትም፡፡ በአገሪቱ አስከፊ ነገር እየሆነ ነው፡፡ አገሬን ወክዬ ጆሃንስበርግ አልገኝም ነው ያሉት ትራምፕ፡፡

ደቡብ አፍሪካ እስካሁን ለትራምፕ ንግግር ምላሽ አልሰጠችም፡፡ በደቡብ አፍሪካ ነጮች ላይ የዘር ማጥፋት ተፈጽሟል የሚለው የአሜሪካ ክስ ውድቅ የተደረገ እና ተዓማኒ ማስረጃ የሚጎድለው መሆኑንም መንግስት ከዚህ ቀደም ገልጻል፡፡

የደቡብ አፍሪካ የወጀል አሃዝ ነጮች ከሌሎች ደቡብ አፍሪካዊያን በተለየ ዒላማ መደረጋቸውን አያሳይም ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ልዩ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ መንግስት ያለ ካሳ ክፍያ መሬት መውሰድ እንዲችል የሚፈቅድ ህግ አጽድቀው ነበር፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe