ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ከኢቢሲ የቦርድ አባልነት ተሰናበቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ላለፉት 3 ዓመታት የብሔራዊ ጣቢያው የኢቢሲ የቦርድ አባል ሆነው የቆዩት ፕሮፌሰር መራራ ጉዲናን ማሰናበታቸው ተሰማ፤
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በቦርድ አባልነት እንዲሰሩ አዳዲስ አባላትን መርጠው ለህዝብ ተወካች ምክር ቤት ያቀረቡ ሲሆን ቀደም ሲል በቦርድ አባልነት ይሰሩ ከነበሩት ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና በተጨማሪ  የቀድሞውን የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኑሮዋን በኡጋንዳ ካምፖላ ያደረገችው ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴን እንዲሁም ዑዝታዝ አቡበከር አህመድን አሰናብተው  በአዳዲስ አባላት ቀይረዋል፤
 ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢቢሲ ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩትን ዶ/ር አለሙ ስሜን አሰናብተው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉን  የሾሙ ሲሆን አንጋፋው የሚዲያ ባለሙያ ዶ/ር ንጉሴ ተፈራን በግል፤ አቶ ዮሱፍ ኢብራሂምን ከአብን፤ አቶ ታረቀኝ ቡልቡልታ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፤ ዶ/ር አብዱልዋላ አብዱላሂን ከዲሞክራሲያ ግንባታ ማዕከል ፤ አቶ ጃፋር ከድርን ከውጭ ግንኙነት ኢንስቲትዩት፤ አቶ መሳፍንት ተፈራን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት፤ ወ/ሮ አመለወርቅ እዝቄኤልን ከትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም  ረዳት ፐፕሮፌሰር ሙና አቡባከር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ሆነው ተሹመዋል፤
ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ፖርቲያቸው ኢፌኮ የሚያወጣቸው መግለጫዎች በኢቲቪ ባለመዘገቡ ተቃውሟቸውን በማሰማት በቦርድ ስብሰባ ላይ መገኘት ካቆሙ  ሁለት ዓመታት ማለፉን ምንጮች ተናግረዋል፤ዛሬ የተሰናበቱት ዘጠኙም የኢቢሲ የቦርድ አባላት ለውጥ አላመጡም በሚል ሲተቹ ቆይተዋል፤
 የኢቢሲ ዘጠኙ የቦርድ አባላት ሹመት የጸደቀው በሶስት የምክር ቤት አባላት ድምጸ ተዐቅቦ ሲሆን ተሻሚዎቹ በምክር ቤቱ ተገኝተው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe