“የሕወሃት የጥፋት ቡድን እኔን አፍኖ ለመያዝ 5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጭ አድርጓል”

<የሕወሃት የጥፋት ቡድን እኔን አፍኖ ለመያዝ 5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጭ አድርጓል…> ፖለቲከኛና ፀሃፊው አንዳርጋቸው ጽጌ።
ከዚህ ወጭ የቀድሞው የደህንነት ሃላፊ ጌታቸው አሰፋ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላሩን በአሜሪካን አገር በራሱ የባንክ አካውንት ማስቀመጡንም መረጃው አለኝ ብለዋል።
ፖለቲከኛው አንዳርጋቸው ጽጌ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ቆይታ አድርገዋል።
ፖለቲከኛው የህወሃት ቡድን አገር እየመራ በነበረበት ወቅት ” አሸባሪ” ተብለው በህወሃት ቡድን የመን ሰንአ ኤርፖርት ላይ ታፍነው በግፍና እንግልት ወደ አገር ቤት መምጣታቸውን ያስታውሳሉ።
በእስራት በቆዩባቸው ዓመታትም በርካታ እንግልትና ስቃይ ደርሶባቸው እንደነበር ገልጸዋል።
በዚህ አጋጣሚ ታስረው በነበረበት ወቅት ራሳቸውን “የኢትዮጵያ መንግስት እስረኛ ሳይሆን የወያኔ እስረኛ” መሆናቸውን ይረዱ እንደነበርም ገልጸዋል።
ቡድኑ በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት እስርቤቶችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የፍትህ ስርዓቱ ላይ ፈላጭ ቆራጭና አፋኝ ስለነበር እንደፈለገ ወንጀል ሲፈጽም መቆየቱንም ያስታውሳሉ።
የህወሃት ቡደን የአገሪቷን ተቋማት በሙሉ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በራሱ ሰዎች ተቆጣጥሮ ግፍና በደል እንዲሁም ዘረፋ ሲያካሂድም ኖሯል ያሉት አቶ አንዳርጋቸው፤ ቡድኑ ብሄራዊ ጥቅምንና ደህንነትን አሳልፎ መስጠት መገለጫው መሆኑን ገልጸዋል።
የጥፋት ቡድኑ አገር እንዲበተን በመጣር በዘርና ማንነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ በማራመድ ሀገራዊ አንድነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያላደረገው ነገር የለም ብለዋል አቶ አንዳርጋቸው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe