ፖላንድ ድንበሯን አቋርጠው የሚገቡ ኢትዮጽያንን ማስጠንቀቋ ተሰማ፡፡ ኢትዮጽያውያኑ ፖላንድ ድንበር ድረስ እስኪ ደርሱ ድረስ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደርጋሉ፡፡
ሀገሪቱን ኢትዮጽያዊያን እና ኤርትራዊያን ቤላሩስን እንደ መሸጋገሪያ በመጠቀም ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ወደ አውሮፓ ለመግባት እንደሚሞክሩ ገልጻለች፡፡ ይህንን መሠረት ያደረገ አዲስ ዘመቻ መጀመሯን አስታውቃለች፡፡
ፖላንድ ኢትዮጽያን ጨምሮ በስድስት ሀገራት ህግ-ወጥ ስደተኞች ላይ ጠንካራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ እንደ ጀመረች የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡
ፖላንድ ከቤላሩስ የምትዋሰንበትን ድንበር በማረቋረጥ ወደ አውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ለመግባት የሚሞክሩ ስደተኞችን ለመከላከል ኢትዮጽያ እና ኤርትራን ጨምሮ ነው በስድስት ሀገራት የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ መጀመሯን ያስታወቀችው፡፡ ኢትዮጽያዊያን እና ኤርትራዎያን ወደ ቤላሩስ በትምህርት ቪዛ ከገቡ በኋላ አደገኛውን የሚባለውን የፖላንድና ቤላሩስን ድንበር አቋርጠው ጀርመንን ጨምሮ ወደ ሌሎች ሀገራት ለመግባት ይሞክራሉ፡፡
ፖላንድ አሁን ድንበሯን በብቃት እየጠበቀች መሆኗን ገልጻ ድንበሩን ለማቋረጥ መሞከር አደገኛ ነው ብላለች፡፡
ኢትዮጽያ፡ኤርትራ፡ሶማሊያ እና ግብጽ የፖላንድ ዘመቻ ይካሄድባቸዋል ተብለው ከተለዩ ሀገራት መካከል ናቸው፡፡
የፓላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራዶስላው ሲኮርስኪ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት በአውሮፓ የተደላደለ ህይወት እንደሚኖራችሁ ቃል የገቡላችሁ ዋሽተዋችኋል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የፖላንድ ድንበር ዘመናዊ የቁጥጥር መሳሪያ የተገጠመለት፡ከ5 ሜትር የሚረዝም ረጅም አጥር ያለው እና አደጋኛ ውሾችም የሚጠብቁት ነው ይህ የሀገራቱ ድንበር፡፡
ፖላንድ ከቤላሩስ ጋር የምጋራው ድንበር ወደ አውሮፓ መግቢያ በር አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል ብላለች፡፡
ፖላንድ አሁን በጀመረችው ዘመቻ ሰዎች ገንዘባቸውንና ህይወታቸውን እንዳያጡ በማሰብ መሆኑን ይፋ አድርጋለች፡፡
ፖላንድ ከቤላሩስ ጋር በምትጋራው 186 ኪሎ ሜትር ላይ አምስት ሜትር ርዝመት ያለው አጥር ገንብታለች ከዚህ ውጭም በአጥሩ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ካሜራዎችን ገጥማለች፡፡/

