ሀማስ አዲስ በቀረበለት የ60 ቀናት ተኩስ አቁም ስምምነት ምክረ ሀሳብ መስማማቱ ተገለጸ

ሀማስ አዲስ በቀረበለት የተኩስ አቁም ስምምነት ምክረ ሀሳብ መስማማቱ ተገለጸ። የፍልስጤሙ ቡድን ሁለት ዓመት ሊደፍን የተቃረበውን ጦርነት ለማስቆም ከአሸማጋዮቹ በኩል የቀረበተትን እቅድ ተቀብያለሁ ስለማለቱ ተሰምቷል። ሃማስ እንደተስማማበት የተገለጸው ይህ እቅድ የ60 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስና በህይወት ያሉ 10 የእስራኤል ታጋቾች እንዲለቀቁ የሚጠይቅ እንደሆነ ተዘግቧል።

የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች ጦርነቱን ለማስቆም አዲስ ተደርጓል በተባለ ዲፕሎማሲያው ግፊት ሀሳቡን ተቀብለዋል ሲል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ምንጮች ነገሩኝ ብሎ ተናግሯል። የሀማስ ሰዎች ከአደራዳሪዎቹ እጅ ዝርዝር መረጃውን ከተቀበሉ በኋላ በእቅዱ ላይ ምንም የሚሻሻል ነገር እንደሌለ ገልጸው ለንግግር ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

በአሜሪካ የሚደገፉት ሁለቱ አሸማጋዮች ግብፅና ኳታር በሰርጡ እየተባባሰ የመጣውን ሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት እየሰራን ነው ብለዋል። ግብፅ እንዳለችው ኳታር ይህ ሃማስ ያለ ማቅማማት ተቀብሎታል የተባለውን ምክረ ሀሳብ ለእስራኤል ልካለች ነገር ግን ከእስራኤል በኩል የተሰጠ ምላሽ አለመኖሩም ተሰምቷል።

እንደ ግብፅ መገናኛ ብዙሃን መረጃ ምክረ ሀሳቡ የ60 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ:በሃማስ እጅ በህይወት አሉ ተብለው ከሚታመኑት 20 ታጋቾች ውስጥ ግማሾቸ እንዲለቀቁ:ፍልስጤማዊያን እስረኞች እንዲለቀቁና የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እንዲሆን የሚል ነው።

ይህ እየተሰማ ያለው የእስራኤል የጸጥታ ካቢኔ ጋዛን ሙሉ በሙሉ ይዞ ዘመቻ ለማድረግ የሚፈቅደውን ውሳኔ ካጸደቀ ከሳምንት በኋላ ነው። ይህ እቅድ በውስጥም በውጭም ተቃውሞ እየተነሳበት ዘልቋል። ሃማስ በኦክቶበር 7 ከወሰዳቸው 251 ታጋቾች ውስጥ 49ኙ አሁንም በእጁ ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 27 የሚሆኑቱ በቡድኑ መገደላቸውን የእስራኤል ጦር መረጃው አለኝ ብሏል። ሀማስ ሁሉንም ታጋቾች ለመልቀቅ ሲስማ እስራኤል የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸውን 150 እስረኞች እንዲሁም ተጨማሪ የ15 ዓመት ፍርደኛ የሆኑ ፍልስጤማዊያንን ለመልቀቅ ትስማማለች ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትንያሁ እስራኤል ሁሉንም ታጋቾቿን በአንድ ጊዜ እንዲለቀቁ የሚደርጉ ስምምነቶችን ትፈጽማለች  ጥርነቱን ለማስቆም ከተቀመጠው አንዱ ቅድመ ሁኔታ መካከልም ይህ ነው ብለዋል።

ሀማስ በጥቅምት 7 በ2023 በእስራኤል ላይ ባደረሰው ድንገተኛ ጥቃት ሳቢያ ከ1ሺ 200 በላይ እስራኤላዊን እንዲሞቱ አድርጓል የተባለ ሲሆን፤ከእነዚህ ውስጥም አብዛኞቹ ንጹሃን ናቸው።

በአንጻሩ እስራኤል እየወሰደችው ባለው እርምጃ ከ60ሺ በላይ ፍልስጤማዊያን ተገድለዋል ሲል የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ይገልጻል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe