በኮረና ቫይረስ ወረርሽን ሳቢያ የአየር መንገዶች ኪሳራ ከቀን ወደ ቀን እያሽቆለቆለ ነው፡፡ በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 90 ከመቶ የሚሆነውን የመንገደኞች በረራ ቢያቋርጥም ፊቱን ወደ ዕቃ ማጓጓዝ በማዞር ስከታማ ስራ እያከናወነ ነው፡፡
Read also:የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአስሩ የአፍሪካ ምርጥ ብራንድ ድርጅቶች ብቸኛው አፍሪካዊ…
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራአስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ሰሞኑን ለሲኤኤን ቴሌቪዥን ሪቻርድ ኮይስት እንደነገሩት አየር መንገዱ ኮረና ከገባ ጀምሮ ያጣው ገቢ ሲሰላ 1 ቢሊዮን ዶላር ማለትም ከ35 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የታይላንድ መንግስት ንብረት ሆነው ታይ ኤርዌይስ በትላንትናው ዕለት በኪሳራ ሳቢያ ስራ ማቆሙን ሲያስታውቅ፤ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ትልቁ አየር መንገድ ላታም ኤር በዛሬው ዕለት በኪሳራ ስራ ማቆሙን አስታውቋል፡፡ ሉፍታንዛ በበኩሉ ከ9 ቢሊዮን ዩሮ ድጎማ ከመንግስት ጠይቋል፤

