ሂሮሺማ ላይ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት የተፈፀመበት 80ኛ ዓመት ተዘከረ

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሽገሩ ኢሺባ  በተገኙበት በሂሮሺማ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ከተለያዩ የዓለም ተወካዮች  ተገኝተዋል። ዩናይትድ ስቴትስ በሂሮሺማ ከተማ የአቶሚክ ቦንብ ከጣለች 80 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በጃፓን ረቡዕ ረፋድ ላይ በጸጥታ ጸሎት ታስቧል።

የሂሮሽማ ከተማ ከንቲባ ካዙሚ ማትሱይ  ዓለም አቀፋዊ “የጦር ሃይል ግንባታ አዝማሚያ እና የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች እሽቅድድም ለሀገር መከላከያ አስፈላጊ ናቸው የሚለውን ሀሳብ” ተችተው አስጠንቅቀዋል “ይህም “አለም አቀፉ ማህበረሰብ ከታሪክ አሳዛኝ ሁኔታዎች ሊማረው የሚገባውን ትምህርት ችላ ማለት ነው” ብለዋል።

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በሄሮሺማ እና ናጋሳኪ ቦምቦች ከተጣለ በኋላ ጃፓን እጅ ሰጥታ መጠናቀቁ ይታወሳል።

ቦምቦቹ ከ200,000 በላይ ሰዎችን ገድለዋል፡፡ የተወሰኑት ወዲያውኑ በደረሰው ፍንዳታ እና ሌሎች በጨረር ህመም እና በተቃጠሉ ቃጠሎዎች ነው የሞቱት። የኑክለሩ ጦር መሳሪያ  ትሩፋት ዛሬም በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ማሰቃየቱ ቀጥሏል።

“አባቴ በፍንዳታው ክፉኛ ተቃጥሏል እና ታውሯል፤ ቆዳው በሰውነቱ ላይ ተንጠልጥሏል – እጄን እንኳን መያዝ አልቻለም” ሲል ከሂሮሺማ የተረፈው ሺንጎ ናይቶ ለቢቢሲ ተናግሯል። ቦምቡ በከተማው ላይ ወድቆ አባቱንና ሁለት ታናናሽ ወንድሞቹን ሲገድል የስድስት ዓመቱ ልጅ ነበር።ሚስተር ናይቶ ታሪካቸውን በሂሮሺማ ከሚገኙ ተማሪዎች ጋር ሲያካፍሉ የዋሉ ሲሆን፣ እነዚህም የአደጋውን ትዝታ ወደ ስነ ጥበብ እየቀየሩ ነው።

እ.ኤ.አ. በ2024 ኒዮን ሂዳንኪዮ የተባለው የጃፓን ቡድን ከአቶሚክ ቦምብ የተረፉ ሰዎች ዓለምን ከኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለማጥፋት ባደረጉት ጥረት የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸንፈዋል።

ከንቲባ ማትሱይ ረቡዕ እለት ባደረጉት ንግግር የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ስርጭትን ለመከላከል እና የኑክሌር ሀይልን በሰላማዊ መንገድ መጠቀምን ለማስፋፋት ያለመ የኒውክሌር መስፋፋት ስምምነት “በችግር አፋፍ ላይ ነው” ብለዋል።

በተጨማሪም የጃፓን መንግስት የኑክሌር ጦር መሳሪያ ክልከላን – እ.ኤ.አ. በ2021 ስራ ላይ የዋለውን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የሚከለክል አለም አቀፍ ስምምነትን እንዲያፀድቅ ጠይቀዋል።

የአቶሚክ ቦምብ ውርስ በጃፓን ዛሬ ቀርቷል። ስምምነቱን ከ 70 በላይ ሀገራት ያፀደቁት ነገር ግን እንደ አሜሪካ እና ሩሲያ ያሉ የኒውክሌር ሃይሎች ተቃውመውታል፡፡ ይህም የኒውክሌር የጦር መሳሪያ መከላከያ ተግባርን ያመለክታል፡፡

ጃፓን ደህንነቷ የሚጠናከረው በአሜሪካ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ነው ስትል ይህን እገዳ ውድቅ አድርጋለች።

የኒውክሌር ጉዳይ በጃፓን ከፋፋይ ነው። ወደ ሰላም መታሰቢያ ፓርክ በሚወስደው ጎዳናዎች ላይ፣ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች እንዲወገዱ የሚጠይቁ ትንንሽ ተቃውሞዎች ተካሂደዋል።

ሌላው በአቶሚክ ቦምብ የተረፈው ሳቶሺ ታናካ በጨረር መጋለጥ ብዙ ካንሰሮችን ያጋጠመው፣ ዛሬ በጋዛ እና ዩክሬን ደም መፋሰስ ማየቱ የራሱን ስቃይ ያመጣል ብሏል።

“የፍርስራሹን ተራራዎች፣ የፈረሱትን ከተሞች፣ ህጻናትና ሴቶች በድንጋጤ ሲሸሹ ማየት ይህ ሁሉ ያሳለፍኩትን ትዝታ ያመጣብኛል” ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። “የሰው ልጅን ብዙ ጊዜ ሊያጠፋው ከሚችል ኒውክሌር ጦር መሳሪያ ጋር አብሮ እየኖረ ነው።”በጣም አንገብጋቢው ቅድሚያ የሚሰጠው በኒውክሌር የታጠቁ ሀገራት መሪዎችን መግፋት ነው። የአለም ህዝቦች የበለጠ ቁጣ ሊሰማቸው፣ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው መጠነ ሰፊ እርምጃ መውሰድ አለባቸው።”

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe