ሂዝቦላ የኔታንያሁን የመኝታ ክፍል በድሮን መምታቱ ተዘገበ

ሄዝቦላህ ከሊባኖስ የተኮሰው ሰው አልባ አውሮፕላን በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ በቂሳሪያ የሚገኘውን መኖሪያ ቤት በመምታቱ በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ጉዳት ማድረሱ ተሰምቷል። አስቀድሞ በእስራኤል ወታደራዊ ኃይሉ ሳንሱር እንዳይታተም የተከለከለው ምስል አሁን ላይ ይፋ የተደረገ ሲሆን የድሮን ተፅእኖ በቤቱ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ያሳያል።

ፍንዳታው በመኝታ ክፍል መስኮት ውስጥ መስታወቱ እንዲሰነጠቅ ያደረገ ሲሆን ወደ ቤቱ ውስጥ ግን አልገባም። በተጠናከረ መስታወት እና ሌሎች መከላከያዎች ምክንያት ወደ ውስጥ ዘልቆ መግባት አልቻለም።የመስታወት ቁርጥራጮች በግቢው ውስጥ በቤተሰቡ የውሃ ዋና ገንዳ ውስጥ እንዳረፉ ተነግሯል። በጥቃቱ ምንም ጉዳት በሰው ላይ አልደረሰም። ኔታንያሁ እና ባለቤታቸው በወቅቱ ቤት ውስጥ እንዳልነበሩም ጄሩሳሌም ፖስት ዘግቧል።ሂዝቦላህ ማክሰኞ በሰጠው መግለጫ “በቂሳርያ በኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ ኢላማ ያደረገውን ኦፕሬሽን ሙሉ በሙሉ ሀላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቋል።
ኔታኒያሁ በበኩላቸው ይህንን ጥቃት የፈፀመ ከባድ አፀፋ ይጠብቀዋል ሲሉ ተደምጠዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe