ሃይንከን ኢትዮጵያ ከፕሮጀክት አስተግባሪ አጋሩ ማህበረ ህይወት ለማህበራዊ ልማት (ኤምኤስዲ) ከተሰኘ መንግሰታዊ ያልሆነ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር በእንስሳት ማድለብ፣ በዶሮ እና በወተት ላም እርባታ የተሰማራ ፕሮጀክቱን ለሁለተኛ ዙር ተጠቃሚዎቹ ዛሬ በይፋ አስረከበ። ፕሮጀክቱ በኮዮ ፈጨ አካባቢ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ለቤተሰቦች የገቢ ማስገኛ በመፍጠር ገቢያቸውን ለማሳደግ ያለመ ነው። የመጀመሪያ ዙር ተጠቃሚዎች ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር ተረክበው ስራ መጀመራቸው የሚታወስ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ በጠቅላላው 33 ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት የተደረገበት ሲሆን 75 አባወራዎችን ማለትም 30 በቂሊንጦ እና 45 በኮዬ ፈጬ የሚገኙ ነዋሪዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ አድርጓል። ተጠቃሚዎቹ በእንስሳት ማድለብ፣ በወተት ተዋጽኦ እና በዶሮ እርባታ የሚሰማሩ ሲሆን በአካባቢው የምግብ ዋስትና እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመፍጠር በንቃት በመሳተፍ የበኩላቸውን አስተዋጾ ያበረክታሉ።
የሃይንከን ኢትዮጰያ የሰስቴይነብሊቲ እና ሲኤስ አር ሃላፊ አቶ ፍቃዱ በሻህ እንደገለጹት የዚህ ፕሮጀክት ዋና ግብ በድሃ ቤተሰቦች ውስጥ የቤተሰብ ገቢን ማሳደግ ነው። ፐሮጀክቱ ለተጠቃሚዎች የእንስሳት፣ የመኖ፣ የእንስሳት ህክምና ድጋፍ እና የምግብ ማቀነባበሪያ ዕውቀት እና ክህሎትን እንዲያገኙ በማድረግ ኑሮአቸውን እና የማህበረሰብ ልማትን እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።
ይህ ፕሮጀክት የገቢ ማስገኛ አቅሞችን ከማሳደግ ባለፈ የሰራ ዕድል ፈጠራ እና ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር ታልሞ የተነደፈ በመሆኑ ሃይንከን ለዘላቂ ማህበረሰብ ልማት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
የሄኒከን ኢትዮጵያ የኮርፖሬት ጉዳዮች ዳይሬክተር ዊሊያም ሚል በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ሃይንከን በተለያዩ ዘርፎች ለማህበረሰቡ የሚያደርገዉን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ሃይንከን ኢትዮጵያ የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን ለህብረተሰቡ በይፋ አስረከበ

