ለሚዲያ ባለሙያዎች በሃገር አቀፍ ደረጃ ዓለም ዓቀፍ የሙያ ምስክርነትን የሚያረጋግጥ አንድ ወጥ መታወቂያ ሊዘጋጅ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች ምዝገባ ፣ የሙያ ማረጋገጫ እና በብሔራዊ ሚዲያ ሽልማት እውቅና ዙሪያ ያተኮረ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ አካሂዷል።
አውደ ጥናቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የጋዜጠኝነት ስራ በታማኝነት፣ በብቃት እና በተጠያቂነት እንዲተገበር ለማስቻል የሚዲያ ባለሙያዎችን ሙያዊ እውቅናን በመስጠት ህጋዊ ለማድረግ ግልፅ የሆኑ መስፈርቶችን በማስቀመጥ ሁለተናዊ ማእቀፍ ለመዘርጋት አላማ ያደረገ መሆኑን ምክር ቤቱ አስታውቋል።
በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙት የምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ ዓለም ዓቀፍ የሙያ ምስክርነትን የሚያረጋግጥ ዲጂታል ስርአቱን የተከተለ የዲጂታል መታወቂያ በሃገር አቀፍ ደረጃ አንድ ወጥ መታወቂያ ለሚዲያ ባለሞያዎች እንደሚዘጋጅ ተናግረዋል።
ምክር ቤቱ ላለፈው አንድ አመት በባለሙያዎች ሲያስጠና የቆየውን ጥናት ከባለድርሻ አካላት ጋር በዛሬው እለት ውይይት ያካሄደ ሲሆን በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የሚያገኙት ህጋዊ ፍቃድ ባለው መገናኛ ብዙሃን ውስጥ በተለያየ ደረጃ የሚሰሩ ጋዜጠኞች ሲሆን በየአመቱ የሚታደስ ይሆናል።
በግል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን የሚያቀርቡ አክቲቪስቶች መታወቂያ አይሰጣቸውም፣
ምክር ቤቱ ሌላው አስጠንቶ ለውይይት ያቀረበው ብሔራዊ የሚዲያ ሽልማት ዝግጅት ሲሆን ስነምግባሩን የጠበቀ ዘገባ የሚሰሩ ባለሙያዎችን በማወዳደር በየአመቱ የመሸለም እቅድ ተነድፋል።
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህራን ተጠንቶ በቀረበው ጥናት ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጋል።

በአሸናፊ በላይ