ሊረዷችሁ የሚችሉ ያልተፃፉ 22 ማህበራዊ ህጎች

  1. አንድን ሰው በተከታታይ ከሁለት ጊዜ በላይ አይደውሉ። ጥሪዎን ካላነሱ፣ የሚያከናውኑት አስፈላጊ ነገር እንዳለ ያስቡ፤
  2. የተበደራችሁትን ገንዘብ፣ የተበደራችሁት ሰው ከማስታወሱ ወይም ከመጠየቁ በፊት መልሱ። ይህ ታማኝነትዎንና ባህሪዎን ያሳያል። ይህ በዣንጥላ፣ እስክሪብቶና የምሳ ዕቃ ላይም በተመሳሳይ መልኩ ይሠራል።
  3. አንድ ሰው ምሳ/እራት ሲጋብዝዎት፣ በሜኑው ላይ ያለውን ውድ ምግብ በጭራሽ አይዘዙ።
  4. ‘ኦህ፣ ገና አላገባህም/ሽም?’ ወይም ‘ልጆች የሉህም/ሽም’ ወይም ‘ለምን ቤት አልገዛህም/ሽም?’ ወይም ‘ለምን መኪና አትገዛም/ዢም?’ አይነት አግባብ ያልሆኑ ጥያቄዎችን አይጠይቁ። በፈጣሪያችሁ! ይህ የእናንተ ችግር አይደለም፤
  5. ከኋላችሁ ለሚመጣው ሰው ሁል ጊዜ በሩን ክፈቱ። ወንድም ይሁን ሴት፣ ትልቅም ይሁን ትንሽ ለውጥ የለውም። በህዝብ ፊት ሰውን በአግባቡ በመያዝ ትንሽ አትሆኑም፤
  6. ከጓደኛ ጋር ታክሲ ከወሰዱና እሱ/እሷ አሁን ከከፈለ/ች፣ በሚቀጥለው ጊዜ ለመክፈል ይሞክሩ፤
  7. የተለያዩ አስተያየቶችን አክብሩ። ለእናንተ 6 የሆነው ነገር በተቃራኒ ላለ ሰው 9 ሆኖ እንደሚታይ አስታውሱ። በተጨማሪም፣ ሁለተኛ አስተያየት ለአማራጭ ጥሩ ነው፤
  8. ሰዎች ሲያወሩ በጭራሽ አያቋርጧቸው። ሀሳባቸውን ገልጸው እንዲጨርሱ ፍቀዱላቸው። ‘ሁሉን ስማ፣ ሁሉን አጣራ’ እንደሚባለው፤ 9 . አንድን ሰው ብትቀልዱበትና እሱ በቀልዱ እየተደሰተበት ካልሆነ ወዲያውኑ አቁሙ፤ ዳግመኛም አታድርጉት። ይህን መቀጠል ግዴለሽ መሆንዎን ያሳያል፤ 10 . አንድ ሰው ሲረዳችሁ “አመሰግናለሁ” ይበሉ።
  9. በአደባባይ አመስግኑ። በግል ተቹ፤
  10. በአንድ ሰው የሰውነት ክብደት ላይ አስተያየት ለመስጠት የሚያበቃ ምንም ምክንያት የለም ማለት ይቻላል። ዝም ብለው፣ “በጣም ታምራለህ/ያምርብሻል” ይበሉ። ስለ ክብደት መቀነስ ማውራት ከፈለጉ፣ እነሱ ራሳቸው ያነሱታል፤
  11. አንድ ሰው በስልካቸው ላይ ፎቶ ሲያሳያችሁ፣ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ አታንሸራትቱ። ቀጥሎ ምን ሊኖር እንደሚችል አታውቁም፤
  12. የስራ ባልደረባችሁ የዶክተር ቀጠሮ እንዳለው/ላት ከነገረዎት/ች፣ ለምን እንደሆነ አይጠይቁ፣ ዝም ብለው “ደህና እንደምትሆን/ኚ ተስፋ አደርጋለሁ” ይበሉ። የግል ህመማቸውን እንዲነግሯችሁ በሚያስገድድ አላስፈላጊ ሁኔታ ውስጥ አታስገቧቸው። እንዲያውቁ ከፈለጉ፣ ያለ የእርስዎ ጠያቂነት ያደርጉታል፤
  13. የጽዳት ሰራተኛውን እንደ ዋና ሥራ አስፈፃሚው (CEO) በተመሳሳይ አክብሮት ይያዙ። ከእናንተ በታች ላለ ሰው ምን ያህል ባለጌ መሆን እንደምትችሉ በማሳየት ማንንም አታስደንቁም፤ ነገር ግን በአክብሮት የምትይዟቸው ከሆነ ሰዎች ያስተውላሉ፤
  14. አንድ ሰው በቀጥታ እያናገረዎት ከሆነ፣ ስልክዎን ማፍጠጥ የትህትና የጎደለው ነው፤
  15. እስካልተጠየቁ ድረስ በጭራሽ ምክር አይስጡ፤
  16. ከረጅም ጊዜ በኋላ ከአንድ ሰው ጋር ሲገናኙ፣ እነሱ ስለእሱ ማውራት ካልፈለጉ በስተቀር፣ ስለ እድሜያቸውና ደሞዛቸው አይጠይቋቸው፤
  17. ነገሩ በቀጥታ የማይመለከታችሁ ከሆነ በራሳችሁ ጉዳይ ላይ አተኩሩ – ዝም ብላችሁ ጣልቃ አትግቡ፤
  18. መንገድ ላይ ከየትኛውም ሰው ጋር እያወሩ ከሆነ የፀሀይ መነፅርዎን ያውልቁ። ይህ የአክብሮት ምልክት ነው። ከዚህም በላይ፣ የአይን ለአይን ግንኙነት እንደ ንግግራችሁ ሁሉ አስፈላጊ ነው፤ 21 . በድሆች መካከል ስለ ሀብታችሁ በጭራሽ አታውሩ። በተመሳሳይ፣ ልጅ በሌላቸው ሰዎች መካከል ስለ ልጆቻችሁ አታውሩ። 22 . ጥሩ መልዕክት ካነበቡ በኋላ “ስለመልዕክቱ አመሰግናለሁ” ለማለት ይሞክሩ። ማድነቅ/ማመስገን የሌላችሁን ነገር ለማግኘት በጣም ቀላሉ መንገድ ነው። እወዳችኋለሁ ! ተዋነይ – Tewanay

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe