ላይፍ ቦይ የእጅ መታጠቢያ ብቻ ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚዘዋወረው መረጃ የተሳሳተ ነው ተባለ

ዩኒሊቨር ኢትዮጽያ ላይፍቦይ ዓለም አቀፍ የእጅ መታጠብ ቀን ህይወቴን ለመጠበቅ “እጄን በውሃ እና በሳሙና እታጠባለሁኝ” በሚል መሪ ቃል በአጼ ነአኩቶ ለአብ ትምህርት ቤት በዛሬው ዕለት አክብሯል።
ላይፍ ቦይ ሳሙና ለእጅ እንጂ ለፊት መታጠብ አይውልም በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተ እና ላይፍ ቦይ ለፊት፣ ለገላ፣ ለእጅ መጠቀም የሚቻል እንዲሁም የአመራረት ሂደቱም ጥራቱን የጠበቀ መሆኑን የዩኒሊቨር ኢትዮጵያ ኮርፖሬት አፊርስ የሆኑት ደግሰው አማኑ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
በዓለም ዙሪያ 190 ሀገራት ውስጥ እየሰራ የሚገኘው ዩኒሊቨር ከፍተኛ ጥራት ያለቸውን አቅምን ባማከለ ሁኔታ ተደራሽ መሆን የሚችሉ የጋራ ንጽህና መጠበቂያ፣ የግል ንጽህና መጠበቂያዎች እና ምግቦችን የሚያመርት ተቋም መሆኑን የዩኒሊቨር ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ጆርጅ ኦስዋንሳ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ በምስራቅ ኢንዱስትሪ ዞን የማምረቻ ፋብሪካውን በይፋ ስራ ከጀመረ በኋላ ላይፍቦይ ሳሙና፣ ኦሞ፣ ክኖር አንኳር፣ ሰንላይት ሳሙናና ዱቄት እንዲሁም ሲግናል እያመረተ ለገበያ እያቀረበ ይገኛል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe