ልጆችዎ ላይ ይጠንቀቁ
ልጆቻችሁን እነርሱ ከሚፈልጉት ይልቅ በራሳችሁ ፍላጎት የመምራት ልማድ አላችሁ? ይህ የብዙ ወላጆች ደካማ ጎን ነው፡፡ በርካታ ወላጆች ‹ልጃቸው ምን መሆን እንዳለበት/እንዳለባት› ለመወሰን ይሽቀዳደማሉ፡፡ ውሳኔያቸውን ልጆች ሳይቀበሉ በሚቀሩ ጊዜ ደግሞ ብጥብጥ ውስጥ መግባት የተለመደ ይሆናል፡፡ በእርግጥ ማንኛውም ወላጅ የልጆቹን ፍላጎት ከማሟላት ጀምሮ አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ ግዴታና ኃላፊቱ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ከተገቢው በላይ የሆነ ጥንቃቄ እያደረጉ ልጆችን ነጻነት ማሳጣትና በውሳኔያቸው መግባት ማለት አይደለም፡፡ የልጆች ውሳኔ ተገቢ ባይሆን እንኳን ውሳኔያቸውን በግዴታ ለማስለወጥ ከመሞከር ይልቅ መመካከር ተገቢ ነው፡፡ ለልጆች ከተገቢው በላይ ጥንqaቄ ማድረግና በእያንዳንዱ የሕይወታቸው ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ መግባትም በራስ የመተማመን ጥንካሬ ያሳጣቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ ማንኛውም ወላጅ ሊከተላቸው የሚገቡ ሁለት መርሆች አሉ፡፡ የመጀመርያው ፍላጎታቸውን ለይቶ ማወቅ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፍላጎታቸው ያለውን ጥቅምና ጉዳት እንዲሁም ፍላጎታቸውን ለማሟላት እንደ ወላጅ ማድረግ ያለበትን ኃላፊነት መወጣት ነው፡፡ እነኚህን መርሆች ተግባራዊ ለማድረግ ግልጽ የሆነ ምክንያታዊ አቀራረብ እንዲሁም ወደ ተግባር መለወጥ የሚችሉ ዝርዝር ዕቅዶች ያሉት አካሔድ ለልጆቻችሁ አዘጋጁላቸው፡፡ ታ ላይ ሙሉ በሙሉ መወሰን የምትችሉት እናንተ ብቻ ናችሁ፡፡
በርካታ ወላጆች የልጆቻቸውን ፍላጎት በመደገፍ በኩል ልዩነቶች ውስጥ ሲገቡና ሁለቱም የየራሳቸውን ግፊቶች ለማድረግ ሲሞክሩ ማስተዋል የተለመደ ነው፡፡ አባት ልጁ የህክምና ባለሙያ እንዲሆን የሚፈልግ ከሆነ፤ እናት የምህንድስና ባለሙያ እንዲሆን ትመኛለች፡፡ ልጅ ደግሞ ከሁለቱም የተለየ የራሱ ፍላጎት አለው፡፡ እነኚህን ሁሉ ፍላጎቶች ማስማማትና አንዱን መምረጥ የሚቻለው ተቀራርቦ በመነጋገር ነው፡፡ ትክክለኛ አቅማቸውን ካለመገንዘብ የእኛን ምርጫ ብቻ እንዲያሟሉ ብለን በምንመርጥላቸው ሥራ ወይም የአኗኗር ዘዬ የሚኖሩ ልጆች ለሥራው የማይመጥን አቅም ስለሚኖራቸው በቀላሉ ለድብርትና ለጫና የመጋለጥ አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት በሥራቸውም ስኬታማ አይሆኑም፡፡ ልጆቻችሁ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ከሆነ፤ እያንዳንዱን ነገር እየሠራችሁ ጥገኝነትን ከምታለማምዷቸው፤ የራሳቸውን ነጻነት ስጧቸው፡፡ አሳዩዋቸው እንጂ አትስሩላቸው፡፡ እንደ ወላጅ ምሯቸው እንጂ ኑሯቸውን ለመኖር አትሞክሩ፡፡ በርካታ ወላጆች ለልጆቻቸው ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄ እስከምን ድረስ መሆን እንዳለበት ካለማወቃቸው የተነሳ የልጆቻቸው የትዳር ሕይወት ውስጥ ገብተው እስከመበጥበጥ ሲደርሱ ይስተዋላል፡፡ ‹ለልጄ ባሏን የምመርጥላት እኔ ነኝ› የሚሉ ወላጆች መኖራቸውን መቼም ሳንሠማ አንቀርም፡፡
ምንጭ፡- yourtango.com
ልጆቻችሁን በራሳችሁ ፍላጎት የመምራት ልማድ አላችሁ?

