ልጆች ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንተርኔት አጠቃቀም እንዲኖራቸው የሚያስችሉ መንገዶች

ወቅቱ ትምህርት ተዘግቶ ተማሪዎች እረፍት የሚያደርጉበት የእረፍት ጊዜ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ታዳጊዎች እና ሕጻናት ኢንተርኔትን ለተለያየ አላማ ይጠቀማሉ፡፡ በመሆኑም ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንተርኔት አጠቃቀም እንዲኖራቸው ወላጆች እና አሳዳጊዎች ሊወስዱ ከሚገቧቸው የጥንቃቄ መንገዶች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው ፡፡
1. የልጆች ተወዳጅ መተግበሪያዎች እና ድረ-ገጾች ላይ ትኩረት ይስጡ
ልጆች በማይገባ ይዘት እንዳይጎዱ (inappropriate content) በማሰብ ኢንተርኔትን ጨርሶ መከልከል አግባብ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ኢንተርኔት ልጆች ለጥያቄያቸው መልስና የሚፈልጉትን እውቀት የሚያገኙበት አንዱ መንገድ ነውና። ነገር ግን የልጆችን የመስመር ላይ ባህሪ መቆጣጠር፤ ለሚወዷቸው መተግበሪያዎች እና ድረ-ገጾች ትኩረት ሰጥቶ እምቅ ጎጂ ይዘት እንደሌላቸው ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
2. በልጆች የመስመር ላይ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍ
አንዳንድ ጊዜ ወላጆች በልጆች የመስመር ላይ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍ አለባቸው። ይህ የልጆችን ፍላጎት ለማወቅ እና በመስመር ላይ አደጋዎችን ለማስወገድ ይረዳል። የግል መረጃቸውን እንዳያጋልጡ፣ አደገኛ ጣቢያዎችን እንዳይከፍቱ ወዘተ… ማስረዳት ያስችላል።
3. በልጆች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ላይ የፀረ-ቫይረስ ፕሮግራም መጫን
ውስን የሳይበር እውቀት ያላቸው ልጆች በአንዳንድ እንግዳ ማገናኛዎች (Links) ሊሳቡ እና ግላዊ መረጃቸውን በማስገባት ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላል። በመሆኑም ወላጆች የልጆችን የኤሌክትሮኒክ መገልገያዎች ከአደጋ ለመጠበቅ የሚያስችሉ መተግበሪያዎችን ወይም ጸረ ቫይረሶችን መጫን ይኖርባቸዋል ።
4. ከልጅዎ ጋር የበይነ መረብ አጠቃቀም እቅድ መፍጠር
ወላጆች እና ልጆች በጋራ በመሆን የኢንተርኔት አጠቃቀም እቅድ ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ልጆች፡-
• መቼና ለምን ያህል ሰዓት በይነ መረብ ላይ እንደሚቆዩ፤
• ምን ዓይነት ይዘቶችን እንደሚያስሱ፤ እና
• በየትኞቹ የበይነ መረብ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ፤
በመጨረሻም በጋራ ያቀዱትን በጋራ መተግበር የሚያስችል የጋራ እቅድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
5. ልጆችዎን በወላጅ መቆጣጠሪያ መተግበሪያዎች ይጠብቁ
በልጆች የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ላይ አስተማማኝ የወላጅ መቆጣጠሪያ መተግበሪያ መጫን በዚህም ጎጂ ይዘትን በመስመር ላይ ማጣራት እና የልጆችን የመስመር ላይ ባህሪ ማስተዳደር ይቻላል።
SourceINSA

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe