መረጃ የማይሰጡ የስራ ኃላፊዎች ከደመወዛቸው እንዲቀንስባቸው የሚያደርግ የመረጃ ነጻነት ማሻሻያ አዋጅ መዘጋጀቱ ተሰማ፡፡
መረጃ የማይሰጡ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የደመወዛቸውን አንድ-ሦስተኛ እንዲቀጡ የሚያደርግ የመረጃ ነጻነት ማሻሻያ አዋጅ እየተዘጋጀ ነው ተባለ፡፡
የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነጻነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 እየተሻሻለ ያለው የመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ ተብሎ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጻል፡፡
በማሻሻያው መሠረት መረጃ ሲጠየቁ አልሰጥም የሚሉ ኃላፊዎች እንደ በፊቱ በተቋም ደረጃ ሳይሆን፤በግለሰብ ደረጃ በህግ ተጠያቂ እንዲደረጉ የሚያስገድድ ነው ተብሏል፡፡
ከዚህ በፊት የነበረው አዋጅ ላይ የተቀመጠው ስልጣን የተሟላ አለመሆኑ፤የመረጃ ነጻነት አፈጻጸምን ደካማ አድርጎት መቆየቱን የህዝብ እንባ ጠባዊ ተቋም ገልጻል፡፡
ለህዝብ በይፋ የማይገለጹ መረጃዎችን በተመለከተ በስራ ላይ ያለው አዋጅ ግልጽ ባለመሆኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ለተቋማቸው ገጽታ በሚል መረጃዎችን የለም ወደ ማለት እንዲያደሉ እንዳደረጋቸውም ተቋሙ ገልጻል፡፡
የመረጃ ነጻነት ድርጊቶችን ማጋለጥና ተቋማትን ተጠያቂ ማድረግ ነው ያለው ተቋሙ በማሻሻያው መሠረት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የተቋማት መረጃዎችን በቀጥታ እንዳይሰጡ የሚያስገድድ ለማድረግ መታሰቡን አስታውቋል፡፡ ሆኖም የህዝብ ግንኙት ባለሙያዎች የተቋማቱ ዋና የመረጃ ምንጭ መሆናቸው እየታወቀ የመስሪያ ቤረቱን የበላይ ኃላፊ ብቻ፡ሚኒስትሮችና ኮሚሽነሮች መረጃ እንዲሰጡ መደረጉ የመረጃው ፍሰት አሉታዊ ተዕጽኖ ሊኖረው እንደሚችል የህግ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
መረጃ የመሰጠት ኃላፊነቱን የተቋሙ ኃላፊ እንዲወስድ መታቀዱ ታውቋል፡፡ ይህንን ኃላፊነት በአግባቡ በማይወጡ ላይ እንደ ተቋም ሳይሆን እንደ ግሰለብ የህግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን እንደሚደረግም የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ገልጻል፡፡
የመጀመሪያ ዕርምጃ የሚሆነው የጹሑፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት ሲሆን ከዚያ ውጭ ደግሞ ደረጃ በደረጃ የደመወዝ እንድ-ሦስተኛ ቅጣት ለመጣል መታቀዱን አስታውቋል፡፡
በስራ ላይ ባለው አዋጅ ተቋማት በጹሑፍ መረጃ ሲጠየቁ በ30 ቀናት መስጠት እንዳለባቸው ተቀምጧል፡፡
በ30 ቀናት የነበረው በ21 ቀናት እንዲሆን፤አስቸኳይ መረጃ ከሆነ ደግሞ ከ10 ቀናት ወደ 48 ስዓት እንዲወርድ ተሻሽሏል፡፡
ጋዜጠኞች የሚዘግቡት ዘገባ ሐሰተኛ ካልሆነና ሆን ብለው ስም ለማጥፋት ሳይሆን እውነቱን ካጋለጡ በፍርድ ቤት ተጠያቂነታቸው እስኪረጋገጥ ድረስ ተጠርጥረው አለመታሰር ወይም ጉዳያቸውን ወጭ ሆነው መከታተል እንዲችሉ የሚደርግ ድንጋጌ በረቂቅ አዋጁ ተካቷል፡፡//

