መንግስት በማይናማር በከፍተኛ የደህንነት ስጋት ውስጥ ያሉ 200 ኢትዮጽያዊያንን ወደ ሀገር ለመመለስ ጥረት ላይ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጽያ መንግስት በማይናማር በከፍተኛ የደህንነት ስጋት ውስጥ ያሉ 200 ኢትዮጽያዊያንን በ10 ቀናት ወደ ሀገር ለመመለስ ጥረት ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡

እነዚሁ ኢትዮጽያዊያን በተደጋጋሚ መንግስት ከስፍራው እንዲያስወጣቸው ሲጠይቁ የቆዩ ናቸው፡፡

በመጭዎቹ 10 ቀናትም 200 ኢትዮጽያዊያን እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

እስካሁን ባለው ሂደትም በማይናማር በአስከፊ ሁኔታ የነበሩ 130 ዜጎችን ማስመለስ እንደተቻለም ገልጻል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሌሎች ሀገራት በተመሳሳይ ሁኔታ የነበሩ 92ሺ ኢትዮጽያዊያንን በ9ወራት ማስመለስ እንደተቻለም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ተነግሯል፡፡

ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ከማድግ ባሻገር ለመብት ጥሰት የተጋለጡ 13ሺ ዜጎች ድጋፍ እንዲያገኙና መብታቸው እንዲከበር የማድረግ ስራ መሰራቱም ተገልጻል፡፡

በተለያዩ ሀገራት ያሉ ኢትዮጽያዊያንን በተመለከተ የትኛውም ሀገር የሚኖር ሚሲዮን ኢትዮጽያዊያን ያሉበትን ሁኔታ መከታተል፡ድጋፍ ማድረግ እና ተባብሮ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe