ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከበጎ ፈቃደኛ ሴት ጋዜጠኞች ፣ ደራሲያንና ምሁራን ጥምረት ጋር በመሆን ” የእኔም ልጆች ናቸዉ ” በሚል
መሪ ቃል ለከፋ ችግር ለተጋለጡ 50 ሺህ ህጻናት የሚውል ልዩ የቤተሰብ ስፖንሰርሺፕ የገቢ ማሰባሰቢያ ማዘጋጀቱን በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገለጸ።
ይህ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ከነገ የካቲት 27 እስከ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚከናወን ተገልጿል።
የችግሩ ስፋትና የመርሃ-ግብሩ መነሻ
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ ምክንያቶች ሳቢያ ከ7 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ከትምህርት ገበታ መለየታቸውን ።
ይህንን አሳሳቢ ሁኔታ ለመቀልበስ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ካለው የረጅም ጊዜ የቤተሰብ ስፖንሰርሽፕ ልምድ በመነሳት በትግራይ
፣ በአማራ ፣ በኦሮሚያ ፣ በሶማሊያ እና በአፋር የሚገኙ ለከፍተኛ ችግር ለተጋለጡ ህጻናት ድጋፍ ለማሰባሰብ ተነስቷል።
ይህንን ጥሪ የተቀበሉ ሴት ጋዜጠኞች ፣ ደራሲያንና ምሁራን ባቋቋሙት ጥምረት አባላትቱ አስቀድመው ከ100 በላይ ህጻናትን በራሳቸው ስፖንሰር ለማድረግ ቃል በመግባት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
በዚህ ሂደት ውስጥ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች የሚገኙ ሲሆን ታዋቂ ግለሰቦች ፣ ቤተሰቦች ማህበራትና ተቋማት የልጆቹን የኑሮ ዋስትና ለመሸፈን ቃል የሚገቡበትም ነው፡፡
ይህ ድጋፍ ህጻናቱ ከቤተሰባቸው ሳይነጠሉ መሰረታዊ ፍላጎቶችን እንዲያገኙ ፣ በትምህርት ገበታው እንዲቆዩና ለቁም ነገር እንዲበቃ፣ በማንነቱ የሚተማመንና ጤናማ ዜጋ ሆኖ እንዲያድግ የሚያስችል ነው።
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ እና የጥምረቱ አባላት መላው ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዚህ ታላቅ ሀገራዊ ንቅናቄ እንዲሁም የበረከት ስራ ላይ አሻራቸውን እንዲያኖሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ይህ ለ15 ቀናት የሚቆየው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በአባይ ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል የቀጥታ ስርጭት ከምሽቱ 12 ሰአት እስከ ንጋቱ 12 ሰአት የሚከናወን ይሆናል።

