ሜታ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የጎለበቱ ስማርት መነጽሮችን ለተጠቃሚዎች እንደሚያቀርብ አስታወቀ

የሬይ-ባን (Ray Ban) ሜታ መነጽሮች በቅርቡ በሕንድ ለተጠቃሚዎች እንደሚቀርቡ ኩባንያው አስታውቋል፡፡
ስማርት መነጽሮቹ እንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ስፓኒሽ እና ጣልያንኛ ቋንቋዎችን መተርጎም ከመቻላቸውም ባሻገር ተጠቃሚዎች ለሚጠይቋቸው ጥያቄ መረጃ መስጠት እና መዚቃ ለማድመጥ ያስችላሉ፡፡
መነጽሮቹ ከኩባንያው የኢንስታግራምና ሜሴንጀር መተግበሪያዎች መልዕክቶችን፣ ፎቶዎችን፣ የድምፅ እና የቪድዮ ጥሪዎችን በቀጥታ መቀበልና መላክ እንደሚያስችሉ ኢንዲያን ኤክስፕረስ ድረ-ገጽ ዘግቧል፡፡
ኩባንያው ሜክሲኮ እና ዩናይትድ አረብ ኤምሬትን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት መነጽሮቹን በቀጣይ ተደራሽ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe