ሞሀመድ ሳላህ ሊቨርፑልን እንደሚለቅ አሳወቀ !

ከዘጠኝ አመታት በኃላ ግብፃዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሞሀመድ ሳላህ በውድድር አመቱ መጨረሻ ከሊቨርፑል ጋር እንደሚለያይ ይፋ አድርጓል።

“ ጊዜው ደርሷል በአመቱ መጨረሻ ሊቨርፑልን እለቃለሁ “ ሲል ሞሀመድ ሳላህ በመልዕክቱ ተናግሯል።

ሞሀመድ ሳላህ በሊቨርፑል ቀሪ የአንድ አመት ኮንትራት ቢኖረውም ክለቡን በነፃ ዝውውር እንደሚለቅ ተገልጿል።

ሊቨርፑል ታሪካዊ ተጨዋቻቸው ሳላህ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር ያለውን ፍላጎት በመደገፍ ፍቃድ እንዲሰጡ ተነግሯል።

ሳላህ በሊቨርፑል የዘጠኝ አመታት ቆይታው በ310 ጨዋታዎች 189 ጎሎችን አስቆጥሮ 93 ለጎል አመቻችቶ አቀብለዋል ሶስት ግዜ የ “PFA” የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ሁለት  የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎች አሸናፊ አንድ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ሶሰት   ካራባኦ ካፕ  አንድ ኤፌ ካፕ አንድ የክለብ አለም ዋንጫ እና አንድ ሱፐር ካፕ ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe