ላለፉት 25 ዓመታት ከፋሽን ሰዎች ታዋቂዎችን እነ ቺኒዋ አቼቤ ፣ አለን ፔተን፣ የሚ አላዴ፣ ብሬንዳ ፋሴ እና ከሰዓሊያን እነ ቼሪ ሳምባ፣ አብዱላሂ ኮንቴ እና ኢብራሂም አል ሳላሂ በተለያዩ
ዓመታት የሸለመው የአፍሪካ ፋሽንና ሥነ-ጥበብ ሽልማት ( AFRICAN FASHION & ART AWARD -AFAA ) ዘንድሮው ከሚሸልማቸው 100 አፍሪካዊያን የፋሽን እና የሥነ-ጥበብ ሰዎች ውስጥ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ ወንድወሰን ከበደ ኾኗል።
ሰዓሊ ወንድወሰን ከበደ ለሽልማቱ ቀጥታ ተመራጭ እንዲሆን ያበቃው፤ በአፍሪካ ስልጣኔ፣ ባህል እና ፓን አፍሪካኒዝም እንዲሁም በኢትዮጵያ ስልጣኔ ፣ ባህል እና ማንነት ላይ በሠራቸው የስዕል ሥራዎች እና በተለያዩ ዓለማት በተሳተፈባቸው ዐውደ ርዕዮች ባገኛቸው እውቅናና ሽልማቶች ነው።
አዘጋጅ ኮሚቴው ላለፉት ሁለት ዓመታት አጠቃላይ የሥነ-ጥበብ ሥራዎቹን፣ የማኅበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴዎቹን እና አህጉር አቀፍና ዓለማቀፍ ተሳትፎውን ካስጠና በኋላ ካለውድድር በቀጥታ ተሸላሚ እንድሆን ውሳኔ መስጠቱን አሳውቋል ።
ሰዓሊ ወንድወሰን ከበደ የሥነ-ጥበብ ስራዎቹን ከኢትዮጵያ ውጭ በቻይና፣ ኳታር፣ ኢኳዶር፣ ኮሎምቢያ፣ ፔሩ፣ ኩባ፣ ግብፅ፣ ፈረንሳይ እና አሜሪካ ያሳየ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደምም በርካታ ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም ዓቀፍ ሽልማቶችን ተቀብሏል።
ሰዓሊ እና የታሪክ ባለሙያ ወንድወሰን፤ በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ ሠዓሊያንና ቀራፂያን ማኅበር ዋና ጸሐፊ ፤ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሥነ-ጥበብ አማካሪ፣ በኢቲ – ሜትሮፖሊታን ጋለሪ ዳይሬክተር እና ኩሬተር፣ የሀገር አማን እና ሆርን ሪቪው መጽሔቶች ካርቱኒስት እና አምደኛ፣ በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የሕክምና ማኅበር አምባሳደር በመሆን እያገለገለ ይገኛል።
የዘንድሮውን የአፍሪካዊያን የፋሽን እና የሥነ-ጥበብ ሽልማት ከNovember 6th – 8th /2024 በዋና ጽሕፈት ቤቱ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያካሂድ አፋ (AFAA) ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

