ሰዎች ChatGptን እንደ ግል ሃኪማቸው አድርገው መውሰድ የለባቸውም ተባለ

በዓለማችን በአንድ ቀን ብቻ ከ2.5 ቢሊዮን በላይ ሰዎች ChatGptን እያማከሩ እንደሆነ ታውቋል፡፡
በዚህ ስዓት በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ካሉት ታዳጊዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት AIን ለስራቸው እንደሚጠቀሙ ጥናቶች ጠቁመዋል፡፡
ሰዎች AIን ለስራቸው ብቻ ሳይሆን በዚህ ወቅት ስለ ፍቅር ግንኙነታቸው፡ስለ ጤናቸው እና ሌሎች ግላዊ ጉዳዮችን ሳይቀር በመጠየቅ እንደሚያማክሩም ታውቋል፡፡
በተደጋጋሚ ከሚጠየቁት ጥያቄዎች ውስጥም ምን ያህል ቆንጆ ነኝ የሚለው እንደሚገኝበትም ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡
ከላይ የተጠቀሰው ቁጥር ሰዎች በዚህ ወቅት ምን ያህል በ AI ጥገኛ መሆናቸውን እንደሚያሳይ ያስረዳል፡፡ AI የሰዎችን ህይወት በማቅለል እንዲሁም ሰዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በማድረግ እረገድ የተመሰከረለት ቢሆንም ነገር ግን በፍጹም አንዳንድ ግላዊ ሚስጥሮችን ለ AI መግለጽ እንደማይገባ እየተገለጸ ነው፡፡
ከእነዚህም መካከል ሰዎች የባንክ አካውንታቸውን፡የሚስጥር ቁጥራቸውን እና የቢሮ ዶክመንቶቻቸውን ለChatGpt ማስገባት እንደሌለባቸው ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
አንድ ጊዜ እነዚህን ሚስጥራዊ መረጃዎች አስገቡ ማለት ከቁጥጥርዎ ውጭ ሆነ እንደ ማለት ነው ሲሉም ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
ሌላኛው ደግሞ የህክምና ጥያቄዎችን ChatGptን ጠይቆ መድሀኒት መውሰድ እጅግ አደገኛ ነው ተብሏል፡፡ በቅርብ የወጡ ጥናቶች ህክምናን ለተመለከቱ ጥያቄዎች ChatGpt የሚሰጣቸው መልሶች በስህተት የተሞሉ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡
ስለሆነም ሰዎች ChatGpt አንዳንድ ከባድ የሆኑ የህክምና ቃላትን ለመረዳት መጠየቅ ይኖርባቸዋል እንጂ ምንም አይነት ምርመራ ሳያደርጉ ChatGptን ብቻ በመጠየቅ መድሃኒት ወደ መውሰድ መግባት የለባቸውም ተብሏል፡፡
ሦስተኛው ህገ-ወጥ እና ወንጀል ነክ ስለሆኑ ጉዳዮችም ChatGptን መጠየቅ አይገባም፡፡
አራተኛው AIን የሰዎችን ውሳኔ በሚጠይቁ ጉዳዮች ላይ አለመጠቀም፡፡ ለምሳሌ፡- የፍቅር ግንኙነቴን ላቋርጠው ወይ? የሚሉ እና መሰል የሰውን ውሳኔዎችን የሚጠይቁ እውነታዎችን AI እንዲወስን ማድረግ ተገቢ አለመሆኑን ባለሙያዎች ያነሳሉ፡፡ ምክንያቱም AI እርሰዎ ያሉበትን እንዲሁም እያለፉበት ያለውን ህይወት ሊረዳው ስለማይችል እንደሆነ በመግለጽ፡፡
በርግጥ AI በርካታ ስራዎችን በዚህ ስዓት ይሰራል፤ጥቅሙም እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሚስጥራዊ ነገሮችን ማጋራት አደጋ እንዳለውና እሱ የሚሰጠንን ምክር ተቀብለን ሁሉንም ነገር ወደ መወሰን አለማምራት የተሻለ እንደሆነ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe