ሳውዲ በዚህ ዓመት ብቻ በሞት ፍርድ የቀጣቻቸው ሰዎች ቁጥር 340 ነው ተብሎ ይፋ ከሆነ በኋላ ሰኞ እለት ተጨማሪ ሦስት ሰዎችን በሞት እንዲቀጡ ወስናለች። ይህም በሀገሪቱ ታሪክ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ይህን ያህል ቁጥር ሲመዘገብ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።
ባለፍ 2024 ሳውዲ በሞት የቀጣቻቸው ሰዎች ቁጥር 338 ነበረ።
በሳውዲ ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር የተገናኘ እንዲሁም በትጥቅ የተደራጀ ዘረፋ በሞት ከሚያስቀጡ ተግባሮች መካከል ናቸው።
ሳውዲ በሞት ከምትቀጣቸው አብዛኛዎቹ ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተገናኘ እንደሆነ ዘገባዎች ያስረዳሉ።
የሞት ቅጣት ውሳኔዎች ከተላለፋባቸው ሰዎች ውስጥ የውጭ ሀገራት ዜጎች ይገኙበታል። ከሀገራቱ ዜጎች መካከል ኢትዮጵያዊያን እንደሚገኙበት ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዚያት ይፋ የሆኑ ሪፖርቶች ያሳያሉ።
ከተያዘው 2025 አጋማሽ በፊት ብቻ ከአደንዛዥ እፅ ጋር በተያያዘ ወንጀል ተከሰው በሞት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው ኢትዮጵያዊያን 7 መሆናቸው ተዘግቦ ነበር። በእርግጥ ሳውዲ በሞት ቅጣት የምትቀጣቸውን የውጭ ሀገር ዜጎች በዝርዝር የማትገልፅ ቢሆንም፤መረጃዎች ግን በመብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች በኩል ይወጣሉ።
ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች የሆኑት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂውማንራይትሶች ሳውዲ በሞት ሊያስቀጡ የማችሉ ወንጀሎችን የፈጸሙ ሰዎችን በሞት ትቀጣለች በማለት ድርጊቱን በተደጋጋሚ ሲተቹትም ይደመጣሉ።//
ሳውዲዓረቢያ ሊጠናቀቅ በተቃረበው የ2025 ዓመት ከፍተኛ የተባለ የሞት ቅጣት ወስናለች ተባለ

