ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቮዳኮም ግሩፕ የውጭ ግንኙነት 2025 ኮንፈረንስ ላይ በሁለት ዘርፎች እውቅና አገኘ፡፡
ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 2 ቀን 2025 ዓ.ም ድረስ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የቮዳኮም ግሩፕ የውጭ ግንኙነት 2025 ኮንፈረንስ ላይ ምርጥ የባለድርሻ አካላት የተሳትፎ አመራር እና ምርጥ የወጣቶች ማጎልበት አጋር በተሰኙ ሁለት ዘርፎች በማሸነፍ እውቅና አግኝተናል። ሽልማቱ ቮዳኮም ከሚንቀሳቀስባቸው ስምንት አገራት መካከል መሪ መሆናችንን አመላክቷል።
በደቡብ አፍሪካ ፋንኮርት ኢን ጆርጅ በተካሄደው ኮንፈረንስ የኢትዮጵያ፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የኬንያ፣ የሞዛምቢክ፣ የታንዛኒያ፣ የግብፅ፣ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የሌሴቶ የቮዳኮም ተወካዮችን ያሰባሰበ ነበር። በተጨማሪም ቮዳፎን ዩኬ፣ ሳፋሪኮም ኬንያ፣ ጂኤስኤምኤ (GSMA) ፣ አማካሪዎች እና የተለያዩ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ተገኝተውበታል።
ዝግጅቱ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ፣ ትብብርን ለማጎልበት እና በቮዳኮም ቡድን ውስጥ ለላቀ አፈጻጽም እውቅና ለመስጠት ያለመ መድረክ ነበር። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እውቅና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እና ወጣቶችን በማብቃት፣ ለዘላቂ ልማት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

