ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በነቀምቴ እና አዋሳኝ ከተሞችን ፈጣኑን 4G ኔትወርክ አስጀመረ

ነቀምቴ እና አዋሳኝ ከተሞችን በፈጣኑ እና አስተማማኙ 4G ኔትወርክ የ07 ሳፋሪኮም ቤተሰብ ማድረጉን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አስታወቀ። ይህ የኔትወርክ ማስፋፊያችን ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለሚደረገው የአገልግሎት ማስፋፊያ እና መላውን ኢትዮጵያ ከዳር እስከ ዳር የማዳረስ ሕልማችን ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ብላል።
በነቀምቴ ከተማ እና ዙርያ የሚቀርበው አገልግሎት በ32 ዘመናዊ የኔትወርክ ማማዎች እና ፋይበር መሰረተ ልማት የሚደገፍ፤ በተጨማሪም 250 የሥራ ዕድሎችን በ5 የሽያጭ ወኪሎች የሚፈጥር እንዲሁም ቢዝነሶችን እና ደንበኞቻችንን በምፐሳ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት አቅርቦት የሚያገለግል ነው።

በተጨማሪ ከኔትዎርክ ማስፋፊያ ሥራዎች በተጨማሪ የትምህርት ዘርፉን በዲጂታል ለማገዝ ዋጋው አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ላፕቶፖች እና ራውተሮችን ከ6 ወራት ገደብ አልባ ዳታ ጋር በነቀምቴ ከተማ ለሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አበርክተል።

ለምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደር፣ ለነቀምቴ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ሥራችን እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን ብላል ሳፋሪኮም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe