የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትፋቅ ከእንግሊዛዊው አሰልጣኝ ስቲቭን ጄራርድ ጋር ሊለያይ መሆኑ ተገልጿል።
እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ስቲቭን ጄራርድ ከአል ኢትፋቅ ጋር በጋራ ስምምነት ለመለያየት መወሰናቸው ተነግሯል።
አል ኢትፋቅ በአሰልጣኝ ስቲቭን ጄራርድ እየተመራ ካደረጋቸው ያለፉት አስራ አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው ሁለቱን ነው።
ክለቡ አሁን ላይ በሊጉ አስራ ዘጠኝ ነጥቦችን በመሰብሰብ አስራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።
“ ራሽፎርድ ከመልበሻ ቤቱ መገለል አለበት “ ስኮልስ
የቀድሞ የቀያይ ሴጣኖቹ ተጨዋች ፖል ስኮልስ ማርከስ ራሽፎርድ ማንችስተር ዩናይትድን መልቀቁ የተሻለ እንደሚሆን ተናግሯል።
“ ራሽፎርድ በባህሪው ምክንያት ብዙ ሰዎችን አንገት አስደፍቷል “ ያለው ፖል ስኮልስ ” አሰልጣኙ ለመናገር የፈለጉትም ያንን ይመስለኛል ” ብሏል።
ስኮልስ አክሎም “ ልምምድ የሚሰራበት መንገድ ፣ የሚያሳየው ነገር እና ባህሪው ለወጣቶች ምሳሌ የሚሆን አይደለም በፍጥነት ከሄደ ጥሩ ይሆናል “ ብሏል።
ማርከስ ራሽፎርድን እንደ አርኣያ የሚመለከቱ ታዳጊዎች በመኖራቸው ምክንያት ” እሱ ከመልበሻ ክፍሉ መባረር አለበት “ ሲል ስኮልስ ጨምሮ ተናግሯል።

