ሶስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በመጪው ጥቅምት በሞስኮ እንደሚካሄድ ተገለፀ

ሩሲያ እና የአፍሪካ ሀገራት በመጪው ጥቅምት 28 እና 29 ቀን 2019 ዓ.ም በሞስኮ ለሚካሄደው ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ዝግጅት እያደረጉ ነው። ይህ ጉባኤ የሩሲያ እና የአፍሪካን ግንኙነት የወደፊት አቅጣጫ ለመቀየስ ከመሪዎች፣ ከመንግስት ባለስልጣናት፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከባለሙያዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ ተሳታፊዎችን ያገናኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ውይይቶቹ በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በሃይል፣ በግብርና እና በምግብ ዋስትና፣ በመሰረተ ልማት፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታላይዜሽን፣ በደህንነት፣ በትምህርት እንዲሁም በሰብአዊ ትብብር ዙሪያ ያተኩራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተመሳሳይ ወቅት የሩሲያ-አፍሪካ የኢኮኖሚ እና የሰብአዊ ጉዳዮች ፎረምም በሩሲያ ዋና ከተማ ይካሄዳል።

ለአፍሪካ ሀገራት፣ ይህ ጉባኤ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን፣ ቴክኖሎጂን እና የንግድ አጋርነቶችን ለመሳብ እንዲሁም ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እድል ይፈጥራል ተብሏል።

በተለይም ኢትዮጵያ ከዚህ ጉባኤ ተጠቃሚ ትሆናለች፤ ምክንያቱም አዲስ አበባ ከሞስኮ ጋር በሃይል፣ በግብርና፣ በትምህርት፣ በኢንቨስትመንት፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ በመሰረተ ልማት እና በንግድ ዘርፎች ያላትን ትብብር ለማስፋት እየሰራች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ይህ በሞስኮ የሚካሄደው ስብሰባ፣ እ.ኤ.አ. በ2019 በሶቺ እና በ2023 በሴንት ፒተርስበርግ ከተካሄዱት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ጉባኤዎች በመቀጠል የሚካሄድ እና የሶስት ዓመት ዑደት ያለውን የጉባኤ ባህል የሚያስቀጥል ነው።

አፍሪካ በአለም አቀፍ ዲፕሎማሲ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ያላት ተጽዕኖ እያደገ በመምጣቱ፣ በጥቅምት ወር የሚካሄደው ጉባኤ ለወደፊት የሩሲያ-አፍሪካ ትብብር ቅርጽ ሊሰጡ በሚችሉ ተጨባጭ ስምምነቶች እና አዳዲስ አነሳሶች ምክንያት ከፍተኛ ትኩረት ይስባል ተብሎ ይጠበቃል።

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe