ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጁ 35 የምርምር ሥራዎችን አቀረበ

ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት በ2018 የትምህርት ዘመን በ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጁትን 35 በሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የምርምር ሥራዎች አቅርቧል።

በተቋሙ ተማሪዎች የተዘጋጁት በቴክኖሎጂ እና በአዕምሮ ጤና ላይ ያተኮሩት የምርምር ስራዎች ለአንድ ወር ያህል ለታዳሚዎች ሲቀረቡ መቆየታቸው ተገልጾአል።

የጥናቶቹ ማጠቃለያ መርሃ-ግብር በዛሬው ዕለት ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. በትምህርት ቤቱ ሁለገብ አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት፤ የትምህርት ባለሙያዎች፣ ወላጆች እና ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል።

ከርእሰ ጉዳዮቹ መካከል ኳንተም ኮምፒውቲንግ እና የሰው ሠራሽ አስተውሎት ተፅዕኖዎች በዋናነት ይገኙበታል ተብሏል። የዲጂታል ዕውቀት፣ ድብርት፣ ራስን ማጥፋትና ስለ ‘እስኪዞፍሬኒያ’ ያለ ግንዛቤም በስፋት ተዳስሰዋል።

ተማሪዎቹ በጥናቶቻቸው የደረሱባቸውን አዳዲስ ግኝቶችና ምክረ ሐሳቦች ለታዳሚዎች አብራርተዋል። በቴክኖሎጂ፣ በአዕምሮ ጤና እና በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የቀረቡት ሥራዎች የብዙዎችን ትኩረት ስበዋል።

የትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር መምህር አንዷለም መላኩ ለአሐዱ እንደገለጹት መርሃ ግብሩ የተማሪዎችን የትንተና ብቃት ያጎለብታል። ይህ ተግባር ተማሪዎች የምርምርና የአቀራረብ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

መምህር አንዱዓለም አክለውም መርሃ-ግብሩ የተማሪዎችን የፈጠራ አቅም ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል። ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ከሚያከናውናቸው መርሃ ግብሮች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe