በሐሰተኛ «መርጌታ» ስም 625 ሺህ ብር ያጭበረበረው ግለሰብ ተያዘ

አብርሀም ሰርኬ የተባለ ተጠርጣሪ ራሱን “መርጌታ” ብሎ በመስየም፣ በዳንሻ ከተማ (ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን) ከሚኖሩ ግለሰብ “እቁብ እንዲደርስህ አደርጋለሁ” በሚል ማታለያ 625 ሺህ ብር አጭበርብሯል።

ተጠርጣሪው ተጨማሪ 300 ሺህ ብር ካልተከፈለው “ቤተሰብህን በመተት አጠፋለሁ” በማለት ተበዳዩን ለአስከፊ ስነ-ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ዳርጎታል።

የዳንሻ ከተማ ፖሊስና የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ ባደረጉት የጋራ ክትትል፣ ተጠርጣሪው ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በሉማሜ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል።
መረጃው የምስራቅ ጎጃም ፖሊስ መምሪያ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe