በመካከለኛው ምሥራቅ ተፅዕኖ ፈጣሪ ለመሆን አልሞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን  አይ 24 ኒውስ የቴሌቪዥን ጣቢያ (i24NEWS) አስታወቀ

በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ጋባዥነት ወደ እስራኤል ያመራው የጋዜጠኞች ቡድን የአይ 24 ኒውስ ጣቢያ የቀጥታ ስርጭት ስቱዲዮችን ተመልክቷል፡፡

ለስድስት ቀናት ጉብኝት በእስራኤል የሚገኘው ከተለያዩ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጣው የጋዜጠኞች ቡድን በመካከለኛው ምሥራቅ ተፅዕኖ ፈጣሪ ለመሆን አልሞ የተቋቋመውን  አይ 24 ኒውስ የቴሌቪዥን ጣቢያ (i24NEWS) መጎብኘት ችሏል፡፡

አይ 24 ኒውስ የቴሌቪዥን ጣቢያ ክ12 ዓመታት በፊት በእንግሊዝኛ ፤በአረብኛና በፈረንሳይኛ ቋንቋዎች እለታዊ ዜናዎችን ክቴላቪቭ የሚያሰራጭ ጣቢያ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፅእኖ የመፍጠር ዓላማ እንዳለው  የጣቢያው ኃላፊዎች አስረድተዋል።

ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ፈጣሪ የመሆን ራዕይ ያለው የቴሌቪቭን ጣቢያው በተለያዩ ሀገራት ያሰማራቸውን ሪፖርተሮችን ጨምሮ ከ400 በላይ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እንዳሉት አስታውቋል።

ከእነዚህ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች መካከል ስድስቱ ቤተ እስራኤላውያን መሆናቸውን የጣቢያው ኃላፊዎች አስረድተዋል።

በዋናነት በመካከለኛው ምሥራቅ መገናኛ ብዙኃን በኩል ስለ እስራኤል የሚነገሩ ሚዛናዊ አይደሉም የሚባሉ  መረጃዎችን ሚዛናዊ የማድረግ እቅድ ይዞ የተቋቋመው ጣቢያው በእስራኤል ውስጥ የሚከሰቱ በፖለቲካ በኢኮኖሚና በቴክኖሎጂ ዘርፍያሉ  እውነታዎችን ለዓለማቀፉ ማኅበረሰብ የማቅረብ እቅድ እንዳለውም ታውቋል።

ከመደበኛ የሳተላይት ስርጭት በተጨማሪ በዲጂታል አማራጮች በርካታ ተከታዮችን ማፍራት የቻለው ጣቢያው በተለየ ሀገራት ሪፖርተሮችን በመመደብ ትኩስ ዜናዎችን ለህብረተሰቡ እያቀረበ መሆኑ ተገልጧል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe