በቬንዙዌላ በመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ2መቶ በላይ መድረሱ ተገለጸ

በቬንዙዌላ ዋና ከተማዋ አቅራቢያ በተከሰተው ሁለት ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2መቶ35 ሲደርስ የቆሰሉት ደሞ 4ሺህ 3መቶ መድረሱ ተገልጿል።
በዋና ከተማዋ ካራካስ አቅራቢያ በምትገኘው ላጉዋራ ከተማ ሰዎች በፈራረሱ ህንጻዎች ስር ሆነው እርዳታ ሲጠይቁ ተደምጠዋል።
አሁን ከተጠቀሰው ቁጥር በተጨማሪም ሌሎች የሞቱ ሰዎች አሉ የሚል ስጋት ሲኖር፥ከአደጋው በኋላ ብዙዎች ቤት አልባ እንደሆኑና ደህንነታቸው ባልተጠበቁ ህንጻዎች ውስጥ እንደሚገኙም ተገልጿል።
የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው በቬንዝዌላ የበዓል ቀን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ብዙ ሰዎች በቤታቸው የሚገኙበትም ዕለት እንደሆነ ተነስቷል።
የመጀመሪያው የመሬት መንቀጥቀጥ 20.3 ኪ.ሜ እና ሁለተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ 10 ኪ.ሜ ጥልቀት እንዳላቸው ተገልጿል።
በርካታ ሀገራት የነፍስ አድን ጥረቶችን ለመርዳት ቃል የገቡ ሲሆን፥ አሜሪካ 1መቶ50 ሚሊየን ዶላር እርዳታ ለመስጠት ቃል ገብታለች።
የዪናይትድ ስቴትስ ጦር የፍለጋ እና የነፍስ አድን ቡድኖችን እና ፈጣን የእርዳታ ስፍራዎችን ለመደገፍ የትራንስፖርት መርከቦችን እና አውሮፕላኖችን እየላከ መሆኑን በመግለጫው ገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe