17 ተቋማት በስራ ላይ በሌሉ ሰዎች ስም ከ408 ሺ 462 ብር በላይ ደመወዝ መክፈላቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር አረጋግጧል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 39ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል። በስብሰባው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ፤ የፌዴራል ተቋማትን የ2016 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርቱ በ16 መስሪያ ቤቶችና በ1 የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በሥራ ላይ ለሌሉ ሰዎች እና ከሥራ ለተሰናበቱ ሰራተኞች ክፍያ መፈፀሙን ገልፀዋል። ችግሩ ለተገኘባቸው ተቋማት ክፍያዎቹ ተመላሽ እንዲደረጉ ማሳሰቢያ መላኩንም ዋና ኦዲተሯ አስታውቀዋል።
በተለያዩ ተቋማት በስራ ላይ ለሌሉ ሰዎች ከ408 ሺህ ብር በላይ ደመወዝ ተከፍሏል፡- የፌዴራል ዋና ኦዲተር

