በማዕከላዊ ቴክሳስ አርብ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 78 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል፡፡ ሌሎች 41 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል፡፡
28 ልጆችን ጨምሮ 78 ሰዎች የሞቱት በኬር ካውንቲ በወንዝ ዳርቻ የሚገኝ የክርስቲያን ሴት ልጆች ካምፕ በጎርፍ በመጥለቅለቁ ነው፡፡
አስር ሴት ልጆችና አንድ የካምፑ ሰራተኛ አሁንም እንደጠፉ ነው፡፡
ባለስልጣናት የሟቾች ቁጥር ከዚህም እንደሚጨምር በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ በሚቀጥሉት ከ24 እና 48 ስዓታት ውስጥ በአካባቢው ተጨማሪ አውሎ ነፋስ ይከሰታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በኬር ካውንቲ ከተገኙ አስክሬኖች መካከል 18 አዋቂዎች እና 10 ህጻናት እስካሁን በይፋ ማንነታቸው አልተለየም ተብሏል፡፡//

