በትራምፕ አስተዳደር ወደ 200ሺ የሚጠጉ ሰራተኞችን ከስራ ውጪ ያደረጉት ኤለን ከስራቸው ለቀቁ

በፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር መንግስታዊ ስልጣን ይዘው ወደ 200ሺ የሚጠጉ ሰራተኞችን ከስራ ውጪ ያደረጉት ኤለን ከስራቸው ለቀቁ፡፡የአሜሪካ የብክነት ቅነሳ ዶጅ የተባለውን መስሪያ ቤት በሃላፊነት መርቷል፡፡በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከስራቸው ያሰናበቱት ቱጃሩ ኤለን መስክ ከመንግስታዊ ሃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡

ኤለን መስክ ትላንት ከስልጣኑ ሲለቅ ፕሬዚዳንት ትራምፕን አመሰግናለሁ ብሏል፡፡ ኤለን በኤክስ ገጹ ላይ የመንግስት ልዩ ሰራተኛ ሆኜ የቆየሁበት ጊዜ አብቅቷል ብሏል፡፡ በፕሬዚዳንት ትራምፕ አላስፈላጊ ወጪዎችን ለመቀነስ ለተሰጠኝ እድል ማመስገን እፈልጋለሁ ሲል ተናግሯል፡፡ የዓለማችን ቁጥር አንዱ ቱጃር መስክ ዶጅን እየመራ እንደመይቆይና ሀላፊነቱ ጊዚያዊ ጊዚያዊ እንደሆነ ሲያስታውቅ ቆይቷል፡፡ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ብክነትን እንድቀንስ እድሉን ስለሰጡኝ አመሰግናለሁ ብሏል፡፡ ኤለን መስክ ብክነት እያሉ የሚጠሩት በአሜሪካ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ አማካኝነት በበሽታ እና በድህነት የሚሞቱ ለእስያ እና ለአፍሪካ ሀገራት በድጋፍ መልክ የሚቀርበውን ገንዘብ ነው፡፡ ዛሬ ዩኤስ አይዲ ከስራ ውጪ መሆን ጋር በተገናኘ በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ ኤለን መስክ ልዩ የመንግስት ሠራተኛ የሚል ሃላፊነት ተሰጥቶት በዓመት 130 ቀናት እንዲሰራ ተፈቅዶለት ነበር፡፡ በያዝነው ግንቦት መገባደጃም 130 ቀናት ይሞላዋል፡፡

ነገር ግን መስክ በትራምፕ የበጀት ረቂቅ አዋጅ እንደተከፋ ባስታወቀ ማግስት ሃላፊነቱን መልቀቁ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

ኤለን መስክ በሃላፊነት በቆየባቸው ጊዚያት ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ የመንግስት ሠራተኞችን ከስራ ለማባረር ባሳየው ቆራጥ ውሳኔ በመላው አሜሪካ የነበረው ተቀባይነት እንዲቀንስ አድርጎታል፡፡

ኤለን መስክ በዚህ ስራ ላይ በቆየባቸው ጊዚያቶች የቴስላ መኪና ሽያጭ 13 በመቶ ቀንሷል፡፡ በተመሳሳይ የቴስላ የአክሲዮን ገበያም 45 በመቶ ወርዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe