በትግራይ ክልል በአስር ወራት ብቻ 48 ግለሰቦች ከ10  እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ

የክልሉ ፍትህ ቢሮ በ10 ወራት ውስጥ ሶስት ተከሳሾች በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት መቀጣቱን ገልፆል።

የትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ ባለፉት አስር ወራት የተለያዩ የቁጥጥርና የህግ ማስከበር ስራዎችን መስራቱ የገለፀ ሲሆን በጥቅሉ 1,450 ተጠርጣሪዎች የሚገኙበት 935 የምርመራ መዝገብ በፖሊስ ተጣርተው ወደ ዓቃቢ ህግ መቅረባቸውን ገልጿል።

ከአጠቃላይ 938 መዝገቦች 144 መዝገቦች ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ፖሊስ የተመለሱ፣ 114 መዝገቦች ብቁ ማስረጃ አልቀረበም በማለት የተዘጉ ሲሆኑ 52 መዝገቦች ደገሞ ስልጣን ወዳለው አካል የተላኩ መሆናቸው ተነግሯል።

በበጀት ዓመቱ ያለፉት አስር ወራት ለቀረቡ የተለያዩ የክስ መዝገቦች እንደየ ክብደታቸው ውሳኔ መሰጠቱ ተገልጾ   ሶስት ተከሳሾች በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት፣48 ተከሳሾች ከ10 ዓመት እስከ 20 ዓመት ፅኑ እስራት፣ 25 ተከሳሾች ከ 10 ዓመት በታች የተቀጡ መሆናቸውን ቢሮው ገልጿል።

ከእስራት ቅጣቱ በተጨማሪ በ19 ተኸሳሾች ላይ ከብር 1000 እስከ ብር 100 ሺ የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ መጣሉም ታውቋል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe