በአለም ዋንጫ ታሪክ ሶስት ለዜሮ እየተመሩ ማሸነፍ የቻሉ ሁለት ሀገራት ብቻ መሆናቸውን ያውቃሉ?

በአራት አመት አንድ ጊዜ የሚካሄደው የአለም ዋንጫ ከተጀመረ አንድ ክፍለዘመን ሊሞላው የአንድ እጅ ጣት እድሜ ብቻ ቀርቶታል::
ብራዚል አምስት ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት ስትመራ፤አውሮፓውያኑ ጀርመን እና ጣልያን አኩል አራት አራት ጊዜ በማሸነፍ ይከተላሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ ታላቅ ድግስ ላይ እስከዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች 3ለ0 እየተመሩ ማሸነፍ የቻሉ ሀገራት ሁለት ብቻ መሆናቸውን የአለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር /ፊፋ/ መዝግቦ የያዘውን ክብረወሰን በድረገጹ ባሰፈረው መረጃ አስታውቋል፡፡
የመጀመሪያዋ ሀገር እ ኤ አ በ1954ቱ የስዊዘርላንድ አለም ዋንጫ የተሳተፈችው ኦስትሪያ ናት፤በወቅቱ አዘጋጇ ስዊዘርላንድ በ20 ደቂዎች ውስጥ ሶስት ጎሎች አከታትላ በተጋጣሚዋ መረብ ላይ በማሳረፍ በሰፊ የግብ ልዩነት መምራት የቻለችበትን ውጤት አስመዘገበች፡፡
ውድድሩ በስዊዘርላንድ አሸናፊነት የሚጠናቀቅም መሰለ፤ነገርግን ኦስትሪያ ከመመራት ተነስታ አቻ ከመሆን ባለፈ ከግማሽ ደርዘን ባለይ ጎሎች አዝንባ 7ለ5 ማሸነፍ ችላለች፡፡
በሻምፒዮናው ምእራብ ጀርመን አሸናፊ በመሆን ዋንጫውን ለመጀመሪያ ጊዜ ስታነሳ ኦስትሪያ በ3ኛነት ማጠናቀቅ ችላለች፡፡
ሌላው እንግሊዝ አዘጋጅታ ራሷ ሻምፒዮን የሆነችበት የ1966ቱ አለም ዋንጫ ነው፤ተረኛ ተጋጣሚዎች ደግሞ ፖርቹጋል እና ከእስያ የተወከለችው ደቡብ ኮሪያ ናቸው፡፡
በወቅቱ ደቡብ ኮሪያ እስከ 2002ቱ የአለም ዋንጫ ድረስ ሩብ ፍጻሜ በመድረስ ከእስያ አህጉር የቀዳማት ሀገር አልነበረም፤በጉዲሰን ፓርክ በተደረገው የፖርቹጋል እና ደቡብ ኮሪያ ጨዋታ ኮሪያ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠረቻቸው ጎሎች 3ለ0 መምራት ቻለች፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ግን ነገሮች መልካቸውን ቀይረው የፖርቹጋሎች ፍጹም የበላይነት ታየ፤አምስት ጎሎች አከታትለው በማስቆጠርም ጨዋታውን 5ለ3 በማሸነፍ በውድድሩ ታሪክ ፊፋ በክብረወሰን የመዘገበውን ሁለተኛውን ታሪክ አጻፉ፡፡
ታሪካዊው ተጨዋች ዩዜቢዮ ዳ ሲልቫ ፔሬራ ደግሞ ከአምስቱ ጎሎች ሁለቱን በማስቆጠር የቁርጥ ቀን ተጫዋችነቱን አሳይቷል፡፡
ዩዜቢዮ በውድድሩ በአጠቃላይ 9 ጎሎች በማስቆጠርም ከፍተኛ ግብ እግቢ በመሆን አጠናቋል፡፡
በበላይነህ ይልማ
SourceAMN

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe