በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት በአንድ በርሜል እስከ $150 ሊደርስ ይችላል ተባለ

በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭት መጠናከሩን ተከትሎ፣ በዓለም ዙሪያ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል።
የኢነርጂ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ፣ ግጭቱ በአጭር ጊዜ ካልተገታ በአሜሪካ አንድ ጋሎን ነዳጅ ከ$5 በላይ፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ደግሞ በአንድ በርሜል እስከ $150 ሊደርስ ይችላል።
ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ በአሜሪካ የአንድ ጋሎን መደበኛ ነዳጅ ዋጋ በ34 ሳንቲም በመጨመር $3.32 ደርሷል።
የዲዝል ዋጋም በተመሳሳይ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን፣ የኳታር ኢነርጂ ሚኒስትር ሳድ ሸሪዳ አል ካቢ በሰጡት ማስጠንቀቂያ ግጭቱ በዚህ ከቀጠለ “በጥቂት ቀናት ውስጥ” በፋርስ ባህረ ሰላጤ የሚገኘው የነዳጅ ምርት ሙሉ በሙሉ ሊቆም እንደሚችልና ይህም የዓለምን ኢኮኖሚ አደጋ ላይ እንደሚጥል ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በመቶዎች የሚቆጠሩ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ ቆመው የሚገኙ ሲሆን፣ ኢንሹራንስ ሰጪዎች ለአካባቢው የሚሰጡትን ዋስትና በመሰረዛቸው እንቅስቃሴው በከፍተኛ ሁኔታ ተገቷል።
የትራምፕ አስተዳደር የመንግስት ዋስትና እና የወታደራዊ አጃቢ ጥበቃ ለማድረግ ቃል ቢገባም፣ ገበያው ግን እስካሁን መረጋጋት አልቻለም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe