በአሜሪካ የቀረበው የሰላም እቅድ ታጋቾች እንዲለቀቁና የእስራኤል ጦር ከያዘው ቦታ ለቆ እንዲወጣ የሚያደርግ ነው

ሃማስ በአሜሪካ የቀረበውን የሰላም ስምምነት ውድቅ የሚያደርግ ከሆነ እስራኤል በምትወስደው ማንኛውም እርምጃ የአሜሪካ ሙሉ ድጋፍ ታገኛለች ሲሉ ትራምፕ ገለጹ፡፡

አሜሪካ የጋዛውን ጦርነት ለመቋጨት ያቀረበችው ባለ 20 ነጥብ እቅድ ጦርነቱን የሚቋጭና ታጋቾችንም እንዲለቀቁ የሚያደርግ ነው፡፡  በዋይት ሐውስ ይፋ የሆነው የሰላም እቅድ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ያለውን ጦርነት የሚያስቆም እንዲሁም በህይወት ያሉትንም፤የሞቱትንም የእስራኤል ታጋቾች እስራኤል ስምምነቱን መቀበሏን ባሳወቀች 72 ስዓታት ውስጥ እንዲለቀቁ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ ሐማስ በ72 ስዓታት ውስጥ 20 በህይወት ያሉ እስራኤላዊያን ታጋቾችን እና በህይወት የሌሉትንም አስክሬናቸውን እንዲያስረክብ ተጠይቋል፡፡

ይህንን እቅድ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፡ሳውዲ አረቢያ፡ኳታር፡ግብጽ፡ዮርዳኖስ፡ቱርክ እና ፓኪስታን በጋራ ባወጡት መግለጫ እቅዱን እንደሚደግፉት አሳውቀዋል፡፡

ሁለቱም ወገኖች ስምምነቱን የሚቀበሉ ከሆነ ሁለት ዓመት ሊደፍን የቀናቶች እድሜ የቀረው ጦርነት ወዲያውኑ ያበቃል እቅዱ እንደሚያስረዳው፡፡

የእስራኤል ሃይሎችም ከፍልስጤማዊኑ መሬት እንዲለቁ ይደረጋሉ፡፡ በአንድ ጊዜ ሁሉም የእስራኤል ታጋቾች ሲለቀቁ፤በምትኩ እስራኤል በእድሜ ልክ ፍርድ ያሰረቻቸውን 250 ፍልስጤማዊያንን ጨምሮ የጋዛው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የታሰሩ 1ሺ700 እስረኛ ፍልስጤማዊያን ነጻ ይደረጋሉ፡፡

ይህ በአሜሪካ የቀረበው የሰላም እቅድ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ፡ታጋቾች እንዲለቀቁና የእስራኤል ጦር ከያዘው ቦታ ለቆ እንዲወጣ የሚያደርግ ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትንያሁ የቀረበውን የሰላም ስምምነት እንደሚደግፉት እርግጠኛ መሆናቸውን ቢናገሩም፡ጠቅላዩም መደገፋቸውን ይፋ ቢያደርጉም፤ሃማስ ይቀበለው አይቀበለው ግን ገና የታወቀ ነገር የለም፡፡

ትራምፕ ሃማስ ይህን የሰላም እቅድ ውድቅ የሚያደርግ ከሆነ እስራኤል በምትወስደው እርምጃ የአሜሪካ ሙሉ ድጋፍ እንደሚኖራት በመግለጽ ቡድኑን አስጠንቅቀዋል፡፡

በዋይት ሐውስ የቀረበው ባለ 21 ነጥብ የሰላም ስምምነት አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ፡በሃማስ እጁ ያሉ ታጋቾች በሙሉ እንዲለቀቁ፤በተመሳሳይ በእስራኤል ታስረው የሚገኙ ፍልስጤማዊያኑም እንዲለቀቁ፡ሃማስ ትጥቁን እንዲፈታ እንዲሁም በዓለም አቀፍ አካላት የሚመራ የሽግግር መንግስት እንዲዋቀር የሚጠይቅ ነው፡፡

የትራምፕ አስተዳደር እና የኔትንያሁ መንግስት ያላቸውን ልዩነት እና ወደፊት በምትመሠረተው የፍልስጤማዊያን ዘገር በሚመለከት ያላቸውን አለመግባባት ጭምር ፈተዋል ተብሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን እቅዱን በመቀበላቸው አመስግነው፤አንድ ላይ መስራት ከቻልን ለበርካታ ዓመታት የዘለቀውን ሞት ማስቀረት እንችላለን ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ከፕሬዝዳንቱ አጠገብ ቆመው የጋራ መግለጫ የሰጡት ኔትንያሁ  የጋዛውን ጦርነት ለመቋጨት ያቀረቡትን የእርሶን እቅድ እደግፋለሁ፤የእኛም የጦርነቱ ዓላማችን ሰላምን ለማምጣት ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ሁሉም ታጋቾችን ወደ ቤታቸው የሚመለሱበት፡የሃማስ ወታደራዊ አቅሙ የሚጠፋበት፤ፖለቲካዊ አመራሩም የሚያከትምበት መሆን አለበት ብለዋል፡፡

የዓረብ እና የሙስሊም አገራት ሃማስ ትጥቁን እንዲፈታ መስማማታቸው ይታወሳል፡፡ ትላንት ፕሬዝዳንት ትራም ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔትንያሁ ጋር በኦቫል ኦፊስ ከአንድ ስዓት በላይ በፈጀ ቆይታቸው ሃማስ እቅዱን የሚቀበልበት ጊዜው አሁን ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe