የከተማ አስተዳደሩ የከተማዋን ገጽታ ለመጠበቅ እና በሽታን ለመከላከል ነው ይህንን የማደርገው ማለቱም ተሰምቷል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ የጎዳና ውሾችን ዘመናዊ በሆነ መንገድ የማምከን ሥራ እንደሚሰራም አያይዞ ገልጻል፡፡
ባለቤት አልባ የጎዳና ላይ ውሾችን የመጠለያ ማዕከል አዘጋጅቶ ወደዚህ ለማስገባት የሚያስችል አዲስ የአሰራር ደንብ ተዘጋጅቶለታል ሲል የአስተዳደሩ የእንስሳት በሽታ መከላከልና ቁጥጥር አስታውቋል፡፡
ይህንን ለማድረግ የሚያስችለው ደንብ በረቂቅ ደረጃ ላይ ያለ ነው የተባለ ሲሆን፤በቅርቡም ወደስራ ይገባል ተብሏል፡፡
ባለቤት አልባ የጎዳና ላይ ውሾችን ወደ መጠለያ ለማስገባት መጀመሪያ የውሻ ባለቤትነት ምዝገባ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡
ይህ የሚደረገው ባለቤት አልባ ውሾችን ለመቀነስ ነው ወደ መጠለያ ከገቡ በኋላ የማምከን ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡//

