በአዲስ አበባ ለአዲሱ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ከ50 ሺ ብር በላይ መጠየቁ አነጋጋሪ ሆነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘገየ በላይነህ አዲሱ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ከዛሬ ጀምሮ መሰጠት መጀመሩን ገለጹ። አዲሱ ሠሌዳ ሀገራዊ የሆኑ ይዘቶችን ያካተተ መሆኑን እና ኮፒ ወይም ፎርጂዲ የማይሠራበት መሆኑንም ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለሥልጣን አገልግሎቱን ለማዘመን ቁጥጥሩን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

ታርጋ ታሪፍ

ለዚህም አዲሱን የተሽከርካሪ ሠሌዳ አጠቃላይ ይዘት አተገባበር ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ሥራዎችን ለማዘመን እንዲሁም ኢትዮጵያን የሚገልጹ መለያዎችን የያዘ እና ዓለም አቀፍ መስፈርቱን የተከተለ ነው ብለዋል። ሠሌዳው የተለያዩ መረጃዎችን የሚይዝ በመሆኑ ለሕግ ማስከበር ሥራ የሚመች፣ ቶሎ የማይበላሽ እና ወጪ ቆጣቢ መሆኑን አብራርተዋል። አሁን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሠራ ያለው አዲስ ለሚገዙ መኪኖች አገልግሎቶች የሚጀመር መሆኑን እና ከዚህ በፊት ሠሌዳ ለሌላቸው አገልግሎቱ በቅርብ እንደሚጀመር ገልጸዋል። ሠሌዳው ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ መሰጠት መጀመሩን እና ተገልጋዮች በተመዘገቡበት ቅደም ተከተል እንደሚወስዱ፤ በክልል ከተሞች ደግሞ በቅርቡ እንደሚጀምር ተገልጿል።

ባለስልጣኑ ወጣ የተባለውና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የወጣወን የዋጋ ታሪፍ እስካሁነ አላረጋገጠመ ወይም አላስተባበለም፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe