በአዲስ አበባ ሰሌዳ ሳይፈታና መንጃ ፈቃድ ሳይወሰድ ቅጣት የሚፈጸምበት አሰራር ተጀምሯል ተባለ

የከተማው ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አሽከርካሪ የደንብ ጥሰት ሲፈጽም ሰሌዳው ሳይፈታበትና መንጃ ፈቃዱም ሳይወሰድበት ቅጣት መፈጸም ተጀምሯል ብሏል፡፡

ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ሰሌዳ ሊፈታ እንደሚችልም ገልጻል፡፡ ለአብነትም አሽከርካሪው ቅጣት ተቀጥቶ የቅጣት ደረሰኙ እጁ ላይ የሚገኝ ከሆነ እንዲሁም መንጃ ፈቃድ ማሳየት ካልቻለ ሰሌዳው ይፈታል፡፡

በተጨማሪ ደግሞ ለመቆም በተከለከለ ቦታ ተሸከርካሪ ከቆመና እና አሽከርካሪው ከሌለ ሰሌዳው ይፈታል፡፡ ሰሌዳን ሳይፈቱ ቅጣት መፈጸም መጀመር ያስፈለገው ለወንጀል የሚያጋልጡበት ጉዳዮች በመኖራቸው እንደሆነም ባለስልጣኑ ገልጻል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe