በአዲስ አበባ ከተማ በ6 ወራት 12,016 የሞት ኩነቶች መመዝባቸውን የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ የ6 ወራት የሲቪል ኩነቶች ምዝገባ ሪፖርት ይፋ ሆኗል:: በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ የነዋሪነት እና የሲቪል ምዝገባ አፈፃፀሞችን የከተማዋ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ገምግሟል። በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ የቀረበው ሪፖርት የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይዟል፡

1.የሞት ምዝገባን በተመለከተ፦ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በድምሩ 12,016 የሞት ኩነቶች ተመዝግበዋል። የምዝገባው ዝርዝር ሁኔታም፦

  • 3,141 የሚሆኑት በወቅቱ የተመዘገቡ፤
  • 2,635 በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የተመዘገቡ፤
  • 6,240 ደግሞ የጊዜ ገደባቸው ካለፈ በኋላ የመጡ ኩነቶች ናቸው። 2.የልደት ምዝገባ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፦ በግማሽ ዓመቱ 236,874 የልደት ምዝገባዎች የተከናወኑ ሲሆን፣ ለዚህ ስኬት በዋነኝነት የተጠቀሰው በትምህርት ቤቶች የተደረገው ንቅናቄ ሲሆን፦
  • 101,519 የሚሆኑት በትምህርት ቤቶች ንቅናቄ የተመዘገቡ ናቸው።
  • 41,194 አዲስ የተወለዱ ህፃናት ምዝገባ የተከናወነ ሲሆን፣
  • 13,974 ህፃናት ደግሞ በተወለዱ በ90 ቀናት ውስጥ ተመዝግበዋል። 3.የጉዲፈቻ ምዝገባ፦ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ 182 የጉዲፈቻ ምዝገባዎች ተከናውነዋል። ከእነዚህም መካከል 99ኙ ወቅታዊ፣ 51ዱ የጊዜ ገደብ ያለፈባቸው እና 19ኙ ደግሞ በዘገየ ምዝገባ የተከናወኑ ናቸው ተብሏል። ኤጀንሲው የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ለማዘመንና ነዋሪዎች ኩነቶችን በወቅቱ እንዲያስመዘግቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በመግለጫው አመልክቷል። ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ21% እድገት አሳይቷል። ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe